Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 41:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሦስቱም ወደ ውስጥ ገባ ያሉ በዙሪያቸው ክፈፍ ያሉአቸው መስኮቶች ነበሩአቸው፤ ግድግዳዎቻቸውም ከወለሉ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት የተለበዱ ነበሩ፤ የመስኮቶቹ መዝጊያዎችም በዚሁ የተሠሩ ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እንዲሁም መድረኮቹና ጠበብ ያሉት መስኮቶች፣ በሦስቱም ዙሪያ ያሉት መተላለፊያዎች፣ ከመድረኩ በላይና ራሱ መድረኩም ጭምር ሁሉም በዕንጨት ተለብዶ ነበር። ወለሉ፣ እስከ መስኮቶቹ ያለው ግንብና መስኮቶቹ ተለብደዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የቤቱ መግቢያዎች፥ ጠባቦቹ መስኮቶች፥ በዙሪያቸው የነበሩ ሦስት መተላለፊያዎች፥ የቤቱ መግቢያ ዙሪያውን ከመሬት ጀምሮ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት ተለብጦ ነበር፤ መስኮቶቹም የተሸፈኑ ነበሩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 መድ​ረ​ኮቹ፥ መስ​ኮ​ቶ​ቹና አዕ​ማዱ፥ በስ​ተ​ው​ስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላ​ሙም በእ​ን​ጨት ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በሦ​ስ​ቱም ዙሪያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ። መቅ​ደ​ሱም በመ​ድ​ረኩ አን​ጻር ከመ​ሬት ጀምሮ እስከ መስ​ኮ​ቶቹ ድረስ በእ​ን​ጨት ተለ​ብጦ ነበር፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም የዐ​ይነ ርግብ ነበሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 መድረኮቹ፥ መቅደሱና በስተ ውስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላሙም በእንጨት ተለብጠው ነበር፥ በሦስቱም ዙሪያ የዓይነ ርግብ መስኮቶች ነበሩ። መቅደሱም በመድረኩ አንጻር ከመሬት ጀምሮ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት ተለብጦ ነበር፥ መስኮቶቹም የዓይነ ርግብ ነበሩ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 41:16
14 交叉引用  

የቤተ መቅደሱ ግንብ ከውስጥ በኩል ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርበው በተሠሩ ሳንቃዎች ተለበደ፤ የወለሉም ጣውላ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር።


ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ከውስጥ ሰፋ፥ ከውጪ ጠበብ ያሉ መስኮቶች ነበሩት፤


የቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል በጥድ እንጨትና በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ሆኖ የዘንባባና የሰንሰለት ቅርጽ ተስሎበት ነበር።


ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የቤተ መቅደሱ መድረክ እስከ ሥር መሠረቱ ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።


ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ክብር ከቤተ መቅደሱ መድረክ ተነሥቶ ከኪሩቤል በላይ ወዳለው ስፍራ ወጥቶ ቆመ።


ማረፊያ ክፍሎቹና ዐምዶቻቸው በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶችና ዐይነ ርግቦች ነበሩአቸው፤ በስተመጨረሻ ያሉትም ክፍሎች በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶች ነበሩአቸው፤ በግድግዳ ዐምዶቻቸውም ላይ የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ነበሩባቸው።


ርዝመቱ ኀምሳ ክንድ ወርዱ ኻያ አምስት ክንድ የሆነው በር ከነመተላለፊያው እንደ ሌሎቹ ቦታዎች መስኮቶች አሉት።


ከዚያም በኋላ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው የቅጽር በር አልፎ ሄደ፤ ደረጃውንም ወጥቶ ከጫፉ የመድረኩን ወለል ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ፤


በሁለቱም በኩል ያሉትን መተላለፊያዎች ጨምሮ በምዕራብ በኩል ያለውን የሕንጻውን ርዝመት ሲለካው አንድ መቶ ክንድ ሆነ። የቤተ መቅደሱ መተላለፊያ፥ ቅዱሱ ስፍራና ወደ ውስጥ ዘልቆ የሚገኘው ቅድስተ ቅዱሳን፥


እንዲሁም በውጪ በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ የውስጥ ክፍል የሚያስገባው ከበር በላይ ያለው ስፍራም ተለብዶ ነበር፤ በውስጠኛውና በመካከለኛው ክፍል ያሉት ዙሪያ ግድግዳዎች ቅርጽ ባለው መለበጃ የተለበዱ ነበሩ።


ኻያ ክንድ የሆነው የውስጥ አደባባይ ታልፎ በውጪው አደባባይ ንጣፍ ትይዩ የተሠሩት ክፍሎች ከፎቅ ወደ ፎቅ እያደጉ ወደ ሦስተኛ ፎቅ ደርሰዋል።


“ሕዝቤ ሆይ! የእኔ ቤት ፈርሶ ሳለ፥ እናንተ ተውበው በተሠሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?


አሁን በመስተዋት እንደምናየው ዐይነት በድንግዝግዝ እናያለን፤ በዚያን ጊዜ ግን በግልጥ እናያለን፤ አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እግዚአብሔር እኔን የሚያውቀኝን ያኽል ሙሉ ዕውቀት ይኖረኛል።


跟着我们:

广告


广告