Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 41:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በሁለቱም በኩል ያሉትን መተላለፊያዎች ጨምሮ በምዕራብ በኩል ያለውን የሕንጻውን ርዝመት ሲለካው አንድ መቶ ክንድ ሆነ። የቤተ መቅደሱ መተላለፊያ፥ ቅዱሱ ስፍራና ወደ ውስጥ ዘልቆ የሚገኘው ቅድስተ ቅዱሳን፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም ከቤተ መቅደሱ በስተጀርባ ከግቢው ትይዩ ያለውን ሕንጻ ለካ፤ ይህም በግራና በቀኝ ያሉትን መተላለፊያዎች የሚጨምር ሲሆን፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር። የውጩ መቅደስና የውስጡ መቅደስ ከአደባባዩ ትይዩ ያለው መተላለፊያ በረንዳ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወደ ኋላውም ባለው በተለየው ስፍራ አንጻር የነበረውን የሕንጻውን ርዝመት በዚህና በዚያ የነበሩትን መተላለፊያዎች ጨምሮ ለካ፥ አንድ መቶ ክንድ ነበር። የቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል፥ የአደባባዩ መተላለፊያዎች፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ወደ​ኋ​ላ​ውም በአ​ለው በልዩ ስፍራ አን​ጻር የነ​በ​ረ​ውን የግ​ቢ​ውን ርዝ​መት፥ በዚ​ህና በዚያ ከነ​በ​ሩት ከግ​ን​ቦቹ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የው​ስ​ጡ​ንም መቅ​ደስ፥ የአ​ዳ​ራ​ሹ​ንም መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎች ለካ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ወደ ኋላውም ባለው በልዩ ስፍራ አንጻር የነበረውን የግቢውን ርዝመት በዚህና በዚያም ከነበሩት ከግንቦቹ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 41:15
13 交叉引用  

የቤታችን ምሰሶ የሊባኖስ ዛፍ ነው፤ ጣራውም በጥድ እንጨት የተዋቀረ ነው።


የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ ነው፤ ዞማው ጠጒርሽም የሐር ጒንጒን የመሰለ ነው። ንጉሡም በሹሩባሽ ውበት ተማርኮአል።


በምዕራብ በኩል በባዶው ቦታ ጫፍ አንድ ሕንጻ አለ፤ የሕንጻው ግድግዳ ውፍረት ዙሪያው አምስት ክንድ፥ ወርዱ ሰባ ክንድ፥ ርዝመቱ ደግሞ ዘጠና ክንድ ነው።


ያ ሰው ቤተ መቅደሱን ሲለካ አንድ መቶ ክንድ ሆኖ አገኘው፤ ከቤተ መቅደሱ በኋላ በኩል ባዶው ቦታውን አቋርጦ በስተ ምዕራብ እስካለው የሕንፃው መጨረሻ ድረስ ሲለካ በአንድነት ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ሆነ።


ከቤተ መቅደሱም በምሥራቅ በኩል ባለው በር ፊት ለፊት ያለው ርዝመት በሁለቱም አቅጣጫ ያሉትን ክፍት ቦታዎች ጨምሮ መቶ ክንድ ሆነ፤


ሦስቱም ወደ ውስጥ ገባ ያሉ በዙሪያቸው ክፈፍ ያሉአቸው መስኮቶች ነበሩአቸው፤ ግድግዳዎቻቸውም ከወለሉ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት የተለበዱ ነበሩ፤ የመስኮቶቹ መዝጊያዎችም በዚሁ የተሠሩ ነበሩ።


እንዲሁም በውጪ በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ የውስጥ ክፍል የሚያስገባው ከበር በላይ ያለው ስፍራም ተለብዶ ነበር፤ በውስጠኛውና በመካከለኛው ክፍል ያሉት ዙሪያ ግድግዳዎች ቅርጽ ባለው መለበጃ የተለበዱ ነበሩ።


ከዚህም በኋላ ያ ሰው በውጭ በኩል ወደሚገኘው አደባባይ ወሰደኝ፤ ከባዶ ቦታ ፊት ለፊት እና በሰሜን በኩል ካለው ሕንጻ ትይዩ ወደነበሩት ክፍሎች አመጣኝ።


በስተ ደቡብ በኩል ደግሞ ከውጪው አደባባይ ግንብ ርዝመት ጐን ለጐን ከባዶ ቦታውና ከሕንጻው ፊት ለፊት ክፍሎች ነበሩ።


ያ ሰው የቤተ መቅደሱን ውስጣዊ ክፍሎች ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፥ በምሥራቁ የቅጽር በር በኩል ወደ ውጪ አወጣኝ፤ ከዚያም በኋላ የውጪውን ክልል ለካ።


ኻያ ክንድ የሆነው የውስጥ አደባባይ ታልፎ በውጪው አደባባይ ንጣፍ ትይዩ የተሠሩት ክፍሎች ከፎቅ ወደ ፎቅ እያደጉ ወደ ሦስተኛ ፎቅ ደርሰዋል።


የሦስተኛው ፎቅ ክፍሎች ከሁለተኛውና ከምድር ቤቱ ክፍሎች የጠበቡ ናቸው። ይህም የሆነበት ምክንያት ፎቆቹ ከፍ ባሉ ቊጥር በረንዳዎቻቸው ሰፋ ስለሚሉና ክፍሎቹን ስለሚያጣብቡአቸው ነው።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለው፦ “አካሄድህ እንደኔ ፈቃድ ቢሆን፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብታደርግ፥ በቤተ መቅደሴ የአስተዳዳሪነትን፥ በአደባባዮቼም የበላይነትን ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መላእክት ጋር በእኔ ፊት መግባትና መውጣት እንድትችል ባለሟልነትን እሰጥሃለሁ።


跟着我们:

广告


广告