ሕዝቅኤል 41:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ያ ሰው ቤተ መቅደሱን ሲለካ አንድ መቶ ክንድ ሆኖ አገኘው፤ ከቤተ መቅደሱ በኋላ በኩል ባዶው ቦታውን አቋርጦ በስተ ምዕራብ እስካለው የሕንፃው መጨረሻ ድረስ ሲለካ በአንድነት ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ሆነ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ከዚያም ቤተ መቅደሱን ለካ፤ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ሲሆን፣ የቤተ መቅደሱ ግቢና ሕንጻ ከነግንቡ ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ሆነ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ቤቱንም ለካው፥ ርዝመቱ መቶ ክንድ ሆነ፥ የተለየው ስፍራ፥ ሕንጻውና ግንቡ አንድ መቶ ክንድ ሆነ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የቤተ መቅደሱንም ርዝመት መቶ ክንድ፥ የልዩውን ስፍራና ግቢውን ከግንቡ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የመቅደሱንም ርዝመት መቶ ክንድ፥ የልዩውን ስፍራና ግቢውን ከግንቡ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 参见章节 |