Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 41:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በምዕራብ በኩል በባዶው ቦታ ጫፍ አንድ ሕንጻ አለ፤ የሕንጻው ግድግዳ ውፍረት ዙሪያው አምስት ክንድ፥ ወርዱ ሰባ ክንድ፥ ርዝመቱ ደግሞ ዘጠና ክንድ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በምዕራብ በኩል ከቤተ መቅደሱ ግቢ ትይዩ የሆነው ሕንጻ ወርድ ሰባ ክንድ ነበር። የሕንጻው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ርዝመቱ ዘጠና ክንድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በባሕር መንገድ በኩል በተለየው ስፍራ አንጻር የነበረው ሕንጻ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። የሕንጻው ግንብ ዙሪያ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱ ደግሞ ዘጠና ክንድ ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በልዩ ስፍራ አን​ጻር የነ​በረ ግቢ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግ​ቢ​ውም ዙሪያ የነ​በረ ግንብ ወርዱ አም​ስት ክንድ፥ ርዝ​መ​ቱም ዘጠና ክንድ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በምዕራብም በኩል በልዩ ስፍራ አንጻር የነበረ ግቢ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግቢውም ዙሪያ የነበረ ግንብ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱም ዘጠና ክንድ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 41:12
6 交叉引用  

ከዚህም በኋላ ያ ሰው በውጭ በኩል ወደሚገኘው አደባባይ ወሰደኝ፤ ከባዶ ቦታ ፊት ለፊት እና በሰሜን በኩል ካለው ሕንጻ ትይዩ ወደነበሩት ክፍሎች አመጣኝ።


በስተ ደቡብ በኩል ደግሞ ከውጪው አደባባይ ግንብ ርዝመት ጐን ለጐን ከባዶ ቦታውና ከሕንጻው ፊት ለፊት ክፍሎች ነበሩ።


ያም ሰው እንዲህ አለኝ፦ “ከቤተ መቅደሱ ባዶ ቦታ ፊት ለፊት በሰሜንና በደቡብ ያሉት ክፍሎች የተቀደሱ ናቸው። የተቀደሱበት ምክንያት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡት ካህናት የተቀደሱ ቊርባኖችን የሚበሉባቸው ቦታዎች ስለ ሆኑ ነው፤ ቦታዎቹም የተቀደሱ በመሆናቸው የእህል ቊርባን፥ የኃጢአት ማስተስረያ ቊርባንና ለበደል የሚቀርብ መሥዋዕትን ያኖሩባቸዋል።


ጸያፍ የሆነ ነገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ርኲሰትን የሚያደርግና ውሸት የሚናገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ወደ እርስዋ የሚገቡ ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፉ ብቻ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告