ሕዝቅኤል 40:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም46 ወደ ሰሜን የሚያመለክተውም ክፍል በመሠዊያው ለማገልገል ኃላፊነት ለተሰጣቸው ካህናት ማረፊያ ነው፤ እነዚህ ሁሉ ካህናት ከሳዶቅ ዘር የተወለዱ ሌዋውያን ሲሆኑ፥ በፊቱ ቆመው እግዚአብሔርን ለማገልገል የተፈቀደላቸው እነርሱ ብቻ ናቸው።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም46 በሰሜን ትይዩ ያለው ክፍል ደግሞ በመሠዊያው ላይ ለሚያገለግሉ ካህናት ነው። እነዚህም የሳዶቅ ልጆች ሲሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ማገልገል የሚችሉ ሌዋውያን እነርሱ ብቻ ናቸው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)46 ወደ ሰሜን የሚመለከተው ቤት መሠዊያውን ለሚጠብቁ ካህናት ነው፤ እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል እንዲያገለግሉት ወደ ጌታ የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)46 ወደ ሰሜንም የሚመለከተው ቤት መሠዊያዉን ለማገልገል ለሚተጉ ካህናት ነው፤ እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል ያገለግሉት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው” አለኝ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)46 ወደ ሰሜንም የሚመለከተው ቤት መሠዊያውን ለማገልገል ለሚተጉ ካህናት ነው፥ እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል ያገለግሉት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው አለኝ። 参见章节 |