Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ከዚህም በኋላ ያ ሰው እኔን ወደ ውስጠኛው አደባባይ አስገባኝ፤ እዚያም ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ በሰሜን የቅጽር በር አጠገብ ወደ ደቡብ የሚያመለክት ሲሆን፥ ሁለተኛው በደቡብ የቅጽር በር አጠገብ ወደ ሰሜን የሚያመለክት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 በውስጠኛው አደባባይ፣ ከውስጠኛው በር ውጭ፣ ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ አንዱ በደቡብ ትይዩ በሰሜን በር በኩል ሲሆን፣ ሌላው በሰሜን ትይዩ በደቡብ በር በኩል ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 በውስጠኛው መግቢያ በውጭው በኩል በውስጠኛው አደባባይ ለሚዘምሩ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከት በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ደቡብም ይመለከት ነበር፤ ሌላው ደግሞ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ደቡብ ይመ​ለ​ከት ነበረ፤ ሌላ​ውም ወደ ደቡብ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ፥ እነሆም፥ ሁለት ቤቶች ነበሩ፥ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከት በር አጠገብ ነበረ፥ መግቢያውም ወደ ደቡብ ይመለከት ነበር፥ ሌላውም ወደ ደቡብ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፥ መግቢያውም ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:44
13 交叉引用  

እነዚህም የዘብ ማረፊያ ክፍሎች ከመተላለፊያው በስተጐን እያንዳንዳቸው ተመሳሳይ ስፋት ነበራቸው፤ በእነርሱ መካከል ያሉትም ግንቦች ሁሉ ተመሳሳይ ውፍረት ነበራቸው።


ከዚያ በኋላ ሰውዬው ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፤ በአደባባዩ ዙሪያ የድንጋይ ንጣፍና ክፍሎች ነበሩ ከንጣፉም ፊት ለፊት ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ።


በምሥራቁ በር እንዳለው ዐይነት በሰሜኑ በር ትይዩ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ በር ነበር፤ ሰውዬው ከአንዱ በር እስከ ሌላው በር ሲለካ አንድ መቶ ክንድ ሆነ።


ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያደርስ ሌላም የቅጽር በር ደግሞ ነበር፤ ያም ሰው ውጪኛውን አደባባይ አቋርጦ አደባባይ እስከዚህ እስከ ሁለተኛው ቅጽር በር ያለውን ስፋት ለካ፤ እርሱም መቶ ክንድ ነበር።


የዘብ የማረፊያ ክፍሎቹ የግድግዳ ዐምዶቹና በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ስፋት እንደ ሌሎቹ ነበር፤ የበሩና የመተላለፊያው ርዝመት ኀምሳ ክንድ ወርዱም ኻያ አምስት ክንድ ነበር፤ በመተላለፊያውም ዙሪያ ሁሉ መስኮቶች ነበሩ።


በውጪው አደባባይ በስተ ሰሜን በኩል ከውስጠኛው የቅጽር በር ጋር የተያያዘ ሌላም ተጨማሪ ክፍል ነበር፤ እርሱም ከአደባባዩ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ወደ መግቢያው ክፍል የሚያስገባ ሌላ በር ነበረው፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ የእንስሶች ሥጋ የሚታጠበውም በዚያ ነበር።


ለጥቃቅን ዕቃዎች ማስቀመጫነት የሚያገለግል ስፋቱ አንድ ጋት የሆነ ክፈፍ በውስጥ በኩል በግድግዳዎቹ ላይ ዙሪያውን ተሠርቶ ነበር፤ በጠረጴዛዎቹም ላይ የመሥዋዕቱ ሥጋ ይቀመጥ ነበር።


አንድ ዘንግ ቁመትና አንድ ዘንግ ወርድ ያላቸው የዘብ ማረፊያ ክፍሎች ነበሩት፤ በማረፊያ ክፍሎቹ መካከል ያለው ርቀት አምስት ክንድ ነው፤ የቅጽሩ በር መግቢያ መድረክ ወደ ውስጥ እስከሚያስገባው መተላለፊያ ጫፍ ድረስ አንድ ዘንግ ነው።


በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊም ዜማ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ በውዳሴና በመዝሙር በሙሉ ልባችሁ ጌታን አመስግኑ፤


የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።


跟着我们:

广告


广告