ሕዝቅኤል 40:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም38 በውጪው አደባባይ በስተ ሰሜን በኩል ከውስጠኛው የቅጽር በር ጋር የተያያዘ ሌላም ተጨማሪ ክፍል ነበር፤ እርሱም ከአደባባዩ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ወደ መግቢያው ክፍል የሚያስገባ ሌላ በር ነበረው፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ የእንስሶች ሥጋ የሚታጠበውም በዚያ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም38 በእያንዳንዱ የውስጥ መግቢያ በር መተላለፊያ በረንዳ አጠገብ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚታጠብበት በር ያለው ክፍል አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)38 በበሮቹ መተላለፊያ አጠገብ በር ያለው ዕቃ ቤት ነበረ፤ በዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያጥቡ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)38 በበሮቹም በግንቡ አዕማድ አጠገብ ዕቃ ቤቱና መዝጊያው ነበሩ፤ በዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያጥቡ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)38 በበሮቹም በግንብ አዕማድ አጠገብ ዕቃ ቤቱና መዝጊያው ነበሩ፥ በዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያጥቡ ነበር። 参见章节 |