Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 መግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ። መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 መተላለፊያ በረንዳው ከውጭው አደባባይ ጋራ ትይዩ ነው፤ የዘንባባ ዛፎች በዐምዶቹ ላይ ተቀርጸዋል፤ እስከ መግቢያው ድረስም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 መተላለፊያዎቹም ወደ ውጭው አደባባይ ይመለከቱ ነበር፤ በግንቡም አዕማድ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር፤ መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 መዛነቢያዎቹም ወደ ውጭው አደባባይ ይመለከቱ ነበር፥ በግንቡም አዕማድ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር፥ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:31
6 交叉引用  

ማረፊያ ክፍሎቹና ዐምዶቻቸው በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶችና ዐይነ ርግቦች ነበሩአቸው፤ በስተመጨረሻ ያሉትም ክፍሎች በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶች ነበሩአቸው፤ በግድግዳ ዐምዶቻቸውም ላይ የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ነበሩባቸው።


በስተ መጨረሻ ያለው ክፍል መስኮቶቹና የተሳሉት የዘንባባ ዛፍ ቅርጾችም ከዚህ በፊት በምሥራቁ የቅጽር በር ከታዩት ጋር ተመሳሳይ መጠን ነበራቸው፤ ወደ እርሱም የሚያመሩ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ በውስጥ መተላለፊያ በስተመጨረሻ ያለው ክፍልም በአደባባዩ ትይዩ ይገኝ ነበር።


ወደዚያም የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች አሉ፤ በውስጥ መተላለፊያ በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ቀጥሎ ይገኛል፤ በሁለቱ በኩል ባሉት የግድግዳ ዐምዶች ላይ ደግሞ የዘንባባ ቅርጾች ተስለውባቸው ነበር።


መግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ በሁለቱም በኩል የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ፥ መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።


የመግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ በሁለቱም በኩል የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ፤ መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።


የመግቢያው ክፍል ርዝመት ኻያ ክንድ፥ ወርዱ ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበር፤ ዐሥር የመወጣጫ ደረጃዎቹም ወደዚያ ያደርሱ ነበር፤ በሁለቱ መወጣጫ ደረጃዎች ጐን ዐምዶች ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告