Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ወደዚያም የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች አሉ፤ በውስጥ መተላለፊያ በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ቀጥሎ ይገኛል፤ በሁለቱ በኩል ባሉት የግድግዳ ዐምዶች ላይ ደግሞ የዘንባባ ቅርጾች ተስለውባቸው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከመተላለፊያ በረንዳው ትይዩ የሆኑ ሰባት ደረጃዎች ወደ መግቢያው በር ያመራሉ፤ ወጣ ወጣ ብለው በሚታዩ ግድግዳዎችም ላይ የዘንባባ ቅርጽ አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ወደ እርሱ የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ መተላለፊያዎቹም በፊት ለፊቱ ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ላይ በዚህና በዚያ በዚህና በዚያ ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ሰባት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በፊቱ ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ አንዱ በዚህ አን​ዱም በዚያ ወገን ሆኖ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ወደ እርሱም የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፥ መዛነቢያዎቹ በፊቱ ነበሩ፥ በግንቡም አዕማድ ላይ አንዱ በዚህ አንዱም በዚያ ወገን ሆኖ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:26
8 交叉引用  

ማረፊያ ክፍሎቹና ዐምዶቻቸው በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶችና ዐይነ ርግቦች ነበሩአቸው፤ በስተመጨረሻ ያሉትም ክፍሎች በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶች ነበሩአቸው፤ በግድግዳ ዐምዶቻቸውም ላይ የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ነበሩባቸው።


በስተ መጨረሻ ያለው ክፍል መስኮቶቹና የተሳሉት የዘንባባ ዛፍ ቅርጾችም ከዚህ በፊት በምሥራቁ የቅጽር በር ከታዩት ጋር ተመሳሳይ መጠን ነበራቸው፤ ወደ እርሱም የሚያመሩ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ በውስጥ መተላለፊያ በስተመጨረሻ ያለው ክፍልም በአደባባዩ ትይዩ ይገኝ ነበር።


የዘብ የማረፊያ ክፍሎቹ የግድግዳ ዐምዶቹና በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ስፋት እንደ ሌሎቹ ነበር፤ የበሩና የመተላለፊያው ርዝመት ኀምሳ ክንድ ወርዱም ኻያ አምስት ክንድ ነበር፤ በመተላለፊያውም ዙሪያ ሁሉ መስኮቶች ነበሩ።


መግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ። መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።


ከዚያም በኋላ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው የቅጽር በር አልፎ ሄደ፤ ደረጃውንም ወጥቶ ከጫፉ የመድረኩን ወለል ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ፤


ይልቅስ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እርሱንም በማወቅ ከፍ ከፍ በሉ፤ ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።


跟着我们:

广告


广告