ሕዝቅኤል 40:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያደርስ ከፍ ብሎ የተሠራ የቅጽር በር ነበር፤ ያም ሰው በሁለቱ የቅጽር በሮች ከመካከል ያለውን ርቀት ለካ፤ እርሱም መቶ ክንድ ሆነ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከዚያም ከታችኛው መግቢያ በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው አደባባይ ፊት ድረስ ያለውን ርቀት ለካ፤ በምሥራቅም ሆነ በሰሜን በኩል ያለው ርቀት አንድ መቶ ክንድ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ከታችኛው በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው አደባባይ ፊት ድረስ ወርዱን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ከታችኛውም በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው አደባባይ ፊት ድረስ ወርዱን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ወደ ምሥራቅና ወደ ሰሜን ለካ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ከታችኛውም በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው አደባባይ ፊት ድረስ ወርዱን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 参见章节 |