Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ማረፊያ ክፍሎቹና ዐምዶቻቸው በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶችና ዐይነ ርግቦች ነበሩአቸው፤ በስተመጨረሻ ያሉትም ክፍሎች በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶች ነበሩአቸው፤ በግድግዳ ዐምዶቻቸውም ላይ የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ነበሩባቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ክፍሎቹ እንደ መተላለፊያ በረንዳዎቹ ከግራና ከቀኝ በኩል ትንንሽ መስኮቶች አሏቸው። በዙሪያው ያሉ መስኮቶች በመግቢያው በር ፊት ለፊት የነበሩ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ክፍል ግራና ቀኝ ግድግዳ ላይ ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾበታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ ትናንሽ መስኮቶች ነበሩአቸው፤ ደግሞም በመተላለፊያው ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በዘበኛ ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ የዓይነ ርግብ መስኮቶች ነበሩባቸው፥ ደግሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፥ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:16
29 交叉引用  

የዋናውን ክፍልና የውስጠኛውን ክፍል ግንቦች በሙሉ በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤


ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፥ ኪሩቤልን፥ የዘንባባ ዛፎቹን፥ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው።


እነርሱንም ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው።


ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ከውስጥ ሰፋ፥ ከውጪ ጠበብ ያሉ መስኮቶች ነበሩት፤


ትይዩ የሆኑት የሕንጻው ሁለት ግንቦች እያንዳንዳቸው በመደዳ ሦስት ሦስት መስኮቶች ነበሩአቸው።


የቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል በጥድ እንጨትና በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ሆኖ የዘንባባና የሰንሰለት ቅርጽ ተስሎበት ነበር።


ደጋግ ሰዎች እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዛፍም ያድጋሉ።


በእያንዳንዱ ማረፊያ ክፍል ፊት ለፊት ከፍታው አንድ ክንድ ውፍረቱም አንድ ክንድ የሆነ ዝቅተኛ ግንብ ነበር፤ ክፍሎቹም የአራት ማእዘን ቅርጽ ያላቸው ሆነው እያንዳንዱ ማእዘን ስድስት ክንድ ርዝመት ነበረው።


ከመግቢያው ጀምሮ እስከ መውጫው ድረስ ያለው የመተላለፊያው ርዝመት ኀምሳ ክንድ ነበር።


ርዝመቱ ኀምሳ ክንድ ወርዱ ኻያ አምስት ክንድ የሆነው በር ከነመተላለፊያው እንደ ሌሎቹ ቦታዎች መስኮቶች አሉት።


ወደዚያም የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች አሉ፤ በውስጥ መተላለፊያ በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ቀጥሎ ይገኛል፤ በሁለቱ በኩል ባሉት የግድግዳ ዐምዶች ላይ ደግሞ የዘንባባ ቅርጾች ተስለውባቸው ነበር።


የዘብ የማረፊያ ክፍሎቹ የግድግዳ ዐምዶቹና በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ስፋት እንደ ሌሎቹ ነበር፤ የበሩና የመተላለፊያው ርዝመት ኀምሳ ክንድ ወርዱም ኻያ አምስት ክንድ ነበር፤ በመተላለፊያውም ዙሪያ ሁሉ መስኮቶች ነበሩ።


ዙሪያውም ኻያ አምስት ክንድ ርዝመትና አምስት ክንድ ወርድ ያላቸው መተላለፊያዎች ነበሩ።


መግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ። መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።


የዘብ ማረፊያ ክፍሎቹ፥ የግድግዳ ዐምዶቹና የመግቢያው ክፍል ስፋት እንደ ሌሎቹ ነበር፤ የበሩና የመተላለፊያው ርዝመት ኀምሳ ክንድ ወርዱም ኻያ አምስት ክንድ ነበር፤ በመተላለፊያውም ዙሪያ ሁሉ መስኮቶች ነበሩ።


መግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ በሁለቱም በኩል የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ፥ መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።


የዘብ ማረፊያ ክፍሎቹ፥ የግድግዳ የዐምዶቹና የመግቢያው ክፍል ስፋት እንደ ሌሎቹ ነበር፤ የበሩ የማረፊያ ክፍል ርዝመት ኀምሳ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ አምስት ክንድ ነበር፥ በመተላለፊያውም ዙሪያ ሁሉ መስኮቶች ነበሩ።


የመግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ በሁለቱም በኩል የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ፤ መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።


አንድ ዘንግ ቁመትና አንድ ዘንግ ወርድ ያላቸው የዘብ ማረፊያ ክፍሎች ነበሩት፤ በማረፊያ ክፍሎቹ መካከል ያለው ርቀት አምስት ክንድ ነው፤ የቅጽሩ በር መግቢያ መድረክ ወደ ውስጥ እስከሚያስገባው መተላለፊያ ጫፍ ድረስ አንድ ዘንግ ነው።


በመለበጃውም ላይ ያለው ቅርጽ የዘንባባ ዛፎችና የኪሩቤል ስዕል ነበር፤ በክፍሉም ዙሪያ የዘንባባና የኪሩቤል ሥዕሎች ተሰባጥረው ተስለውበታል፤ እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊቶች ነበሩት፤


በግድግዳዎቹ ላይ እንደተቀረጸው በተቀደሰው ስፍራ በር ላይም ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ተቀርጸው ነበር። በመግቢያው ክፍል ፊት ለፊት በስተውጪ ከእንጨት የተሠራ አጎበር ነበር።


በመግቢያው ክፍል ግድግዳዎች፥ በሁለቱም በኩል ወደ ውስጥ ገባ ያሉ መስኮቶች የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ነበሩ።


ከዚያም አልፎ ወደ ውስጠኛው ክፍል ገባ፤ ወደ እርሱ የሚያስገባውንም መተላለፊያ ሲለካው ርዝመቱ ሁለት ክንድ ወርዱ ስድስት ክንድ ሆነ፤ በግራና ቀኝ የሚገኙትም ግንቦች የእያንዳንዱ ውፍረት ሰባት ክንድ ሆነ።


ኻያ ክንድ የሆነው የውስጥ አደባባይ ታልፎ በውጪው አደባባይ ንጣፍ ትይዩ የተሠሩት ክፍሎች ከፎቅ ወደ ፎቅ እያደጉ ወደ ሦስተኛ ፎቅ ደርሰዋል።


በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ፥ በዕብራይስጥ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ የምንጭ ኲሬ ነበረ፤ በዙሪያውም አምስት ከላይ ክዳን ያላቸው መተላለፊያዎች ነበሩ።


አሁን በመስተዋት እንደምናየው ዐይነት በድንግዝግዝ እናያለን፤ በዚያን ጊዜ ግን በግልጥ እናያለን፤ አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እግዚአብሔር እኔን የሚያውቀኝን ያኽል ሙሉ ዕውቀት ይኖረኛል።


ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችን አየሁ፤ እነርሱ ከሕዝብና ከነገድ፥ ከወገንና ልዩ ልዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሁሉ የተውጣጡ ነበሩ፤ እነዚህ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ነበር፤


跟着我们:

广告


广告