Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነዚህም የዘብ ማረፊያ ክፍሎች ከመተላለፊያው በስተጐን እያንዳንዳቸው ተመሳሳይ ስፋት ነበራቸው፤ በእነርሱ መካከል ያሉትም ግንቦች ሁሉ ተመሳሳይ ውፍረት ነበራቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በምሥራቁ በር ግራና ቀኝ መጠናቸው እኩል የሆነ ሦስት ሦስት የዘብ ቤቶች ነበሩ፤ በመካከላቸው ወጣ ወጣ ብለው የሚታዩትም ግንቦች ተመሳሳይና እኩል ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የምሥራቁ በር ጓዳዎች በዚህ በኩል ሦስት በዚያ በኩል ደግሞ ሦስት ነበሩ፥ ሦስቱም እኩል ስፋት ነበራቸው፤ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል እኩል ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የም​ሥ​ራ​ቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦ​ስ​ቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ በኩ​ልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የምሥራቁም በር የዘበኛ ጓዳዎች በዚህ በኩል ሦስት በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፥ ለሦስቱም አንድ ልክ ነበረ፥ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:10
6 交叉引用  

የበሩን መግቢያ ሲለካ ወርዱ ዐሥር ክንድ ርዝመቱ ደግሞ ዐሥራ ሦስት ክንድ ሆኖ አገኘው።


ግራና ቀኝ ያሉት ሦስቱ የዘብ ማረፊያ ክፍሎችና የግድግዳ ዐምዶች እንዲሁም በስተመጨረሻ ያለው ክፍል በምሥራቁ የቅጽር በር በኩል ከታዩት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ልክ ነበራቸው፤ የቅጽር በሩ ጠቅላላ ርዝመት ኀምሳ ክንድ፥ ወርዱ ኻያ አምስት ክንድ ነበር።


የዘብ የማረፊያ ክፍሎቹ የግድግዳ ዐምዶቹና በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ስፋት እንደ ሌሎቹ ነበር፤ የበሩና የመተላለፊያው ርዝመት ኀምሳ ክንድ ወርዱም ኻያ አምስት ክንድ ነበር፤ በመተላለፊያውም ዙሪያ ሁሉ መስኮቶች ነበሩ።


ከዚህም በኋላ ያ ሰው እኔን ወደ ውስጠኛው አደባባይ አስገባኝ፤ እዚያም ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ በሰሜን የቅጽር በር አጠገብ ወደ ደቡብ የሚያመለክት ሲሆን፥ ሁለተኛው በደቡብ የቅጽር በር አጠገብ ወደ ሰሜን የሚያመለክት ነበር።


አንድ ዘንግ ቁመትና አንድ ዘንግ ወርድ ያላቸው የዘብ ማረፊያ ክፍሎች ነበሩት፤ በማረፊያ ክፍሎቹ መካከል ያለው ርቀት አምስት ክንድ ነው፤ የቅጽሩ በር መግቢያ መድረክ ወደ ውስጥ እስከሚያስገባው መተላለፊያ ጫፍ ድረስ አንድ ዘንግ ነው።


跟着我们:

广告


广告