Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ያንንም ከፈጸምክ በኋላ ተዛውረህ በቀኝ ጐንህ በመተኛት እንደገና የይሁዳን በደል አርባ ቀን ትሸከማለህ፤ ይህም እነርሱን በምቀጣበት በእያንዳንዱ ዓመት ልክ ይሆናል ማለት ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ይህን ከፈጸምህ በኋላ ደግሞ በቀኝ ጐንህ ተኝተህ የይሁዳን ቤት ኀጢአት ትሸከማለህ፤ ለእያንዳንዱ ዓመት አንድ አንድ ቀን በማድረግ አርባ ቀን መድቤብሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነዚህንም በፈጸምህ ጊዜ ድጋሚ በቀኝ ጐንህ ትተኛለህ፥ የይሁዳንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ፥ አንድን ዓመት እንደ አንድ ቀን አድርጌ አርባ ቀን ሰጥቼሃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እነ​ዚ​ህ​ንም በፈ​ጸ​ምህ ጊዜ በቀኝ ጎንህ ትተ​ኛ​ለህ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ኀጢ​አት አርባ ቀን ትሸ​ከ​ማ​ለህ፤ አን​ዱን ቀን አንድ ዓመት አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እነዚህንም በፈጸምህ ጊዜ በቀኝ ጐድንህ ትተኛለህ፥ የይሁዳንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ፥ አንድን ዓመት አንድ ቀን አድርጌ አርባ ቀን ሰጥቼሃለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 4:6
7 交叉引用  

በኃጢአታችሁ ምክንያት አርባ ዓመት ሙሉ ትሠቃያላችሁ፤ ይህም ምድሪቱን ለማጥናት በቈያችሁበት አርባ ቀን ልክ አንዲቱ ዕለት አንድ ዓመት ትሆንባችኋለች፤ በዚያን ጊዜ እኔን መቃወም ምን እንደሚያመጣባችሁ ትገነዘባላችሁ።


ሴቲቱ በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ የታላቅ ንስር ክንፎች የሚመስሉ ሁለት ክንፎች ተሰጡአት፤ እዚያም ከእባቡ ፊት ርቃ ሦስት ዓመት ተኩል በእንክብካቤ ተይዛ ትጠበቅ ነበር።


የትዕቢትና የስድብ ቃል የሚናገርበት አፍ ለአውሬው ተሰጠው፤ አርባ ሁለት ወር በሥልጣን እንዲሠራም ተፈቀደለት።


ለዚህ ሰዓትና ለዚህ ቀን፥ ለዚህ ወርና ለዚህ ዓመት የተዘጋጁት አራቱ መላእክት የሰውን ዘር አንድ ሦስተኛ እንዲገድሉ ተፈቱ።


跟着我们:

广告


广告