Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 39:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ጎግና ሠራዊቱ፥ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተሰለፉ የጦር ጓደኞቹ ሁሉ ሞተው በእስራኤል ተራራዎች ላይ ይወድቃሉ፤ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ እንዲሆን አደርገዋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አንተና ወታደሮችህ ሁሉ፣ ከአንተም ጋራ ያሉ ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ። ነጣቂ አሞሮችና የዱር አራዊት ይበሏችሁ ዘንድ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አንተ፥ ወታደሮችህና ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ ሁሉ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አን​ተና ጭፍ​ሮ​ችህ ሁሉ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉ ሕዝብ በም​ድረ በዳ ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለሚ​ና​ጠቁ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊ​ትም መብል አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፥ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 39:4
14 交叉引用  

የሠራዊት አምላክ እንዲህ ሲል ምሎአል፥ “ያቀድኩት ነገር ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል፤ የወሰንኩትም ነገር ሥራ ላይ ይውላል።


አሦራውያንን ለእስራኤል በሰጠኋት ምድሬ ላይ እደመስሳቸዋለሁ፤ በተራሮቼም ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ ሕዝቤንም ከአሦራውያን የአገዛዝ ቀንበርና ከነበረባቸውም ከባድ ሸክም ነጻ አወጣቸዋለሁ።


እኔ እግዚአብሔር አራት ክፉ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ወስኛለሁ፤ ስለዚህ በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውን ውሾች ይጐትቱታል፤ ወፎች ሥጋቸውን ይበሉታል፤ የተረፈውን አራዊት ይግጡታል፤


በዚያን ቀን እግዚአብሔር በሞት የሚቀጣቸው ሰዎች ሬሳ ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ይረፈረፋል፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ ሰብስቦ የሚቀብራቸው አያገኙም፤ ስለዚህ እንደ ጥራጊ በሜዳ ላይ ተጥለው ይቀራሉ።


አንተንና የወንዞችህን ዓሣዎች ሁሉ ወደ በረሓ እወረውራችኋለሁ፤ ሬሳህም ተነሥቶ ሳይቀበር በመሬት ላይ ወድቆ ይቀራል፤ ለወፎችና ለአራዊትም ምግብ እንዲሆን አደርገዋለሁ።


“እንግዲህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ በፈራረሱ ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ በእርግጥ ይገደላሉ ብዬ ያስጠነቀቅኋቸው መሆኑን ገልጠህ ንገራቸው፤ በገጠር የሚኖሩ የአራዊት ምግብ ይሆናሉ፤ በየተራራውና በየዋሻው ተደብቀው ያሉትም በመቅሠፍት ያልቃሉ፤


ተራራዎችን ሁሉ በተገደሉ ሰዎች ሬሳ እሸፍናለሁ፤ በጦርነት የተገደለውም ሬሳ ኰረብቶቻችሁና ሸለቆዎቻችሁን ወንዞቻችሁንም ሁሉ ይሸፍናል፤


በተራሮቼ ሁሉ በጎግ ላይ ሰይፍ እንዲመዘዝ አደርጋለሁ፤ የያንዳንዱም ሰው ሰይፍ ጓደኛውን ይበላል።


በአውላላ ሜዳ ላይ ወድቀው ይቀራሉ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ፈረሰኞች ወደፊት እየገፉ የሚያብረቀርቅ ሰይፋቸውንና የሚያብለጨልጭ ጦራቸውን ያነሣሉ፤ ብዙ ሰዎች ስለ ተገደሉ ሬሳዎች ተከምረዋል፤ ከሬሳውም ብዛት የተነሣ በዚያ የሚያልፍ ሰው ሁሉ ይደናቀፋል።


跟着我们:

广告


广告