Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 39:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አቅጣጫውን አስለውጬ ሩቅ ከሆነው ከሰሜን አገር ገፋፍቼ በእስራኤል ተራራዎችም ላይ እንዲዘምት አደርገዋለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፤ እንዲሁም እጐትትሃለሁ፤ ከሩቅ ሰሜን አምጥቼ በእስራኤል ተራሮች ላይ እሰድድሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እመልስሃለሁ፥ እመራሃለሁ፥ ከሰሜን ዳርቻ አወጣሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች እወስድሃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እመ​ራ​ሃ​ለሁ፤ ከሰ​ሜ​ንም ዳርቻ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እመልስሃለሁ፥ እነዳህማለሁ፥ ከሰሜንም ዳርቻ እጐትትሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች አመጣሃለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 39:2
8 交叉引用  

ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ። የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ ኀፍረት ይድረስባቸው።


ጢስ በነፋስ በኖ እንደሚጠፋ አብንናቸው፤ ሰም በእሳት ቀልጦ እንደሚያልቅ ክፉዎችም ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ!


በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


“የሰሜን መሳፍንትና ሲዶናውያን እዚያ ናቸው፤ በሥልጣናቸው ተመክተው ሽብር ቢነዙም እንኳ ከተገደሉት ጋር በውርደት ወደ ሙታን ዓለም ወርደዋል፤ በሰይፍ ተገድለው ኀፍረታቸውን በመከናነብ ከወረዱት ጋር በእግዚአብሔር ሳያምኑ ተጋድመዋል።


በስተ ሰሜን በኩል ርቀህ ከምትኖርበት ስፍራ ሁሉም በፈረስ ላይ የሚቀመጡትን የብዙ ሕዝቦች ታላላቅ ሠራዊትን መርተህ ትመጣለህ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሜሼክና የቱባል ሕዝብ ገዢ በሆነው በጎግ ላይ ትንቢት ተናገርበት፤ በእርሱም ላይ የተነሣሁ መሆኔን ንገረው።


ከዚያም በኋላ እርሱን መትቼ ቀስቱን ከግራ እጁ፥ ፍላጻውንም ከቀኝ እጁ አስጥለዋለሁ።


“ጊዜው ሲደርስ የግብጽ ንጉሥ በሶርያ ንጉሥ ላይ አደጋ ይጥልበታል፤ ሆኖም የሶርያ ንጉሥ በሠረገሎች፥ በፈረሶችና በመርከቦች በመጠቀም በብርቱ ጦርነት ይቋቋመዋል፤ እንደ ጐርፍ ውሃ በመጠራረግ ብዙ አገሮችን ይወራል።


跟着我们:

广告


广告