Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 39:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ በእስራኤል ምድር በሚገኘው፥ ከሙት ባሕር በስተ ምሥራቅ ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ውስጥ፥ ለጎግ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም ከብዛቱ የተነሣ መተላለፊያ መንገዱን ይዘጋል፤ ጎግና ሠራዊቱ ሁሉ በዚያ ይቀበራሉ፤ ስለዚህም ያ ሸለቆ ‘የጎግ ሠራዊት ሸለቆ’ ተብሎ ይጠራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ ‘በዚያ ቀን ሰዎች በምሥራቅ በኩል ወደ ባሕሩ በሚጓዙበት ሸለቆ፣ ለጎግ የመቃብር ስፍራ በእስራኤል እሰጠዋለሁ። ጎግና ሰራዊቱ ሁሉ በዚያ ስለሚቀበሩ፣ የተጓዦችን መንገድ ይዘጋሉ፤ ስለዚህም የሐሞን ጎግ ሸለቆ ይባላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በዚያም ቀን በእስራኤል፥ በባሕሩ በምሥራቅ በኩል ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ስፍራ እሰጠዋለሁ፤ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ስለሚቀበሩ፥ የመንገደኞች መተላለፊያ ይዘጋል፤ “የሐሞን-ጎግ ሸለቆ” ተብሎ ይጠራል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “በዚ​ያም ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በባ​ሕር ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ል​ፉ​በ​ትን ሸለቆ፥ የመ​ቃ​ብ​ርን ስፍራ ለጎግ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ል​ፉ​ት​ንም ይከ​ለ​ክ​ላል፤ በዚ​ያም ጎግ​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ይቀ​ብ​ራሉ፤ የሸ​ለ​ቆ​ው​ንም ስም የጎግ መቃ​ብር ብለው ይጠ​ሩ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፥ የሚያልፉትንም ይከለክላል፥ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ይቀብራሉ፥ የሸለቆውንም ስም ሐሞንጎግ ብለው ይጠሩታል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 39:11
10 交叉引用  

ጓጒንቸሮቹም ሁሉ በየስፍራው ተከመሩ፤ ምድሪቱም በግማት ተሞላች።


“የሰው ልጅ ሆይ! በማጎግ ምድር የሚገኙት የሜሼክና የቱባል ሕዝቦች ገዢ የሆነውን ጎግን በመቃወም ትንቢት ተናገርበት፤


ስለዚህም ከየስፍራው የማገዶ እንጨት መሰብሰብም ሆነ፥ ከየጫካውም ዛፍ መቊረጥ አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም ወድቆ የቀረውን የጦር መሣሪያ ሁሉ ሰብስበው ማንደድ ይችላሉ፤ ቀድሞ የበዘበዙአቸውንና የዘረፉአቸውን አሁን በተራቸው መበዝበዝና መዝረፍ ይችላሉ፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ያንን ሁሉ ሬሳ ቀብረው ምድሪቱን እንደገና ለማጽዳት ሰባት ወራት ይፈጅባቸዋል።


በሀገሪቱም ውስጥ ሲዘዋወሩ የሰው ዐፅም በሚያገኙበት ጊዜ በጐኑ ምልክት አድርገውበት ያልፋሉ፤ መቃብር ቆፋሪዎችም መጥተው በሐሞን ጎግ ሸለቆ ይቀብሩታል።


“የምሥራቁ ድንበር በደማስቆና በሐውራን መካከል አልፎ በዮርዳኖስ በኩል፥ በጊልዓድና በእስራኤል ምድር መካከል አልፎ ወደ ሙት ባሕርና እስከ ታማር ድረስ ነው። ይህም የምሥራቁ ድንበር ይሆናል።


በሥጋ አምሮት የሞቱትን ሕዝብ እዚያ ቀብረዋቸው ስለ ነበር የዚያ ስፍራ ስም “የምኞት መቃብር” ተባለ፤


ወሰኑም ከሴፋም ተነሥቶ ከዓይን በስተምሥራቅ በኩል ወደ ሪብላ ይቀጥልና በገሊላ ባሕር በስተ ምሥራቅ ወዳሉት ኮረብታዎች ይደርሳል።


አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ሳለ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ቀርበው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ይጋፉ ነበር።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ጥብርያዶስ ወደሚባለው ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ።


跟着我们:

广告


广告