Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 38:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዚህም ዐይነት ታላቅነቴንና ቅድስናዬን አሳያለሁ፤ በብዙ ሕዝቦችም ዘንድ ራሴን አሳውቃለሁ፤ ከዚያ በኋላ እነርሱ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በዚህም ታላቅነቴንና ቅድስናዬን አሳያለሁ፤ በብዙ ሕዝቦች ፊት ራሴን አሳውቃለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” ’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ታላቅ እሆናለሁ፥ እቀደሳለሁም፥ በብዙ አሕዛብ ዐይን የታወቅሁ እሆናለሁ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ታላቅ እሆ​ና​ለሁ፤ እቀ​ደ​ስ​ማ​ለሁ፤ እመ​ሰ​ገ​ና​ለ​ሁም፤ በብዙ አሕ​ዛ​ብም ዐይን የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ታላቅ እሆናለሁ እቀደስማለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 38:23
17 交叉引用  

እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።


እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።


የታላላቅ መንግሥታት ሕዝቦች ያከብሩሃል፤ በጨካኞች መንግሥታት ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ይፈሩሃል።


ተበታትናችሁ ከነበራችሁባቸው አገሮች ሕዝቦች መካከል አውጥቼ በምሰበስባችሁ ጊዜ መልካም መዓዛ እንዳለው ዕጣን እቀበላችኋለሁ። ሌሎች ሕዝቦች እያዩ በእናንተ መካከል ቅድስናዬን እገልጣለሁ።


ለቀድሞ አባቶቻችሁ እንደምሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ወደ እስራኤል መልሼ በማመፃችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


ለሕዝብዋም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፦ እኔ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ በእናንተ ላይ በማደርገው ድርጊት ሕዝቦች ያመሰግኑኛል፤ ፍርዴን ተግባራዊ በማደርግበትና ቅድስናዬን በምገልጥበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያን ከተበታተኑበት ከተለያዩ አሕዛብ መካከል በምሰበሰብበት ጊዜና ሌሎች ሕዝቦች እያዩ ቅድስናዬን በሕዝቤ መካከል በምገልጥበት ጊዜ ተመልሰው ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።


በሕዝቦች መካከል ተሰድቦ የነበረውን፥ ማለት እናንተ አሰደባችሁት የነበረውን የታላቁን ስሜን ቅድስና አሳያለሁ፤ ከዚያ በኋላ በእናንተ አማካይነት በእነርሱ ፊት ቅድስናዬን በምገልጥበት ጊዜ ሕዝቦች እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።


ቤተ መቅደሴ በመካከላቸው ለዘለዓለም እንዲኖር በማደርግበት ጊዜ፤ ለእኔ እስራኤልን ለራሴ የተለየ ሕዝብ የማደርግ መሆኔን አሕዛብ ያውቃሉ።”


ጅማትና ሥጋ በመስጠት ቆዳ አለብሳችኋለሁ፤ በውስጣችሁም እስትንፋስ አስገብቼ እንደገና በሕይወት እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።’ ”


በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ትመጣባቸዋለህ፤ ጎግ ሆይ፥ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ እንድትመጣ አደርግሃለሁ፤ ይህንንም የማደርገው በአንተ አማካይነት ቅድስናዬን በፊታቸው በምገልጥበት ጊዜ ሕዝቦች እንዲያውቁኝ ነው።’ ”


በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሬሳውን በመቅበር ይተባበሩአቸዋል፤ የእኔ ክብር በሚገለጥበት ቀን ለእነርሱም ክብር ይሆንላቸዋል፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ክብሬን በሕዝቦች መካከል እገልጣለሁ፤ ሕዝቦችም ሁሉ ተግባራዊ ያደረግኹትን ፍርዴንና እነርሱን የቀጣሁበትን ኀይሌን ያያሉ።


እነርሱን ከሕዝቦች መካከል ስመልሳቸውና ከጠላቶቻቸው አገሮችም ብዙ ሕዝቦች እያዩ ስሰበስባቸው በእነርሱ አማካይነት ቅድስናዬን እገልጣለሁ።


ቅዱስ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል ዘንድ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ስሜ እንዲሰደብ አልፈቅድም፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቦች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ መሆኔን ያውቃሉ።”


跟着我们:

广告


广告