Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 37:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እኔም በዚያ ከእነርሱ ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ማደሪያዬ ከእነርሱ ጋራ ይሆናል፤ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ማደሪያዬ በላያቸው ላይ ይሆናል፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፥ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ማደ​ሪ​ያ​ዬም በላ​ያ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ማደሪያዬም በላያቸው ላይ ይሆናል፥ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 37:27
12 交叉引用  

በዚያን ጊዜ ሕጌን ይፈጽማሉ፤ ሥርዓቴንም ሁሉ ያከብራሉ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።


ይህንንም የማደርገው የእስራኤል ሕዝብ ወደ እኔ የሚያደርሰውን መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይስቱና በበደላቸው ሁሉ ዳግመኛ ራሳቸውን እንዳያረክሱ ነው፤ በዚህም ከጸኑ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ። እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


ከዚያም በኋላ ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ እናንተ ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።


ዳግመኛ በጣዖቶቻቸው፥ በአጸያፊ ነገሮቻቸው፥ ወይም በሌሎች ኃጢአቶቻቸው ራሳቸውን አያረክሱም፤ ከወደቁበት ክሕደት አውጥቼ አነጻቸዋለሁ። በዚያን ጊዜ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።


ሕዝቤን በምድሪቱ ላይ እመሠርታለሁ፤ እንዲበለጽጉም አደርጋቸዋለሁ፤ ‘ምሕረት አይደረግላችሁም’ የተባሉትን ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ የተባሉትንም ‘ሕዝቤ ናችሁ’ እላቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘አንተ አምላካችን ነህ’ ይሉኛል።”


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በመካከላችን ኖረ፤ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ እንዳለው ያለውን ክብሩን አይተናል።


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።


ሁሉን የሚችል ጌታ አምላክና በጉ የእርስዋ መቅደስ ስለ ሆኑ በከተማይቱ ውስጥ መቅደስ አላየሁም፤


እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤


ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሆነው ሌሊትና ቀን በመቅደሱ ያገለግሉታል፤ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውም መጠለያቸው ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告