Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አኗኗራቸውና ሥራቸው ሁሉ መጥፎ ስለ ነበረ ፈረድኩባቸው፤ በባዕዳን አገሮችም እንዲበተኑ አደረግሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በአሕዛብ መካከል በተንኋቸው፤ እነርሱም በየአገሩ ተበታተኑ፤ እንደ ጠባያቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ወደ መንግሥታት በተንኋቸው ወደ አገሮችም ተዘሩ፤ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ወደ አሕ​ዛ​ብም በተ​ን​ኋ​ቸው፤ ወደ ሀገ​ሮ​ችም ዘራ​ኋ​ቸው፤ እንደ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውና እንደ በደ​ላ​ቸ​ውም መጠን ፈረ​ድ​ሁ​ባ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ወደ አሕዛብም በተንኋቸው ወደ አገሮችም ተዘሩ፥ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:19
15 交叉引用  

“አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእናንተ ለእስራኤላውያን የምላችሁ ይህ ነው፤ በክፉ ሥራችሁ እያንዳንዳችሁን እቀጣለሁ፤ ስለዚህ ከምታደርጉት ክፋት ተመለሱ፤ አለበለዚያ ኃጢአታችሁ ያጠፋችኋል።


ሕዝብሽን ወደየአገሩና ወደየሕዝቡ እበትናለሁ፤ ክፉ ሥራሽም እንዲያከትም አደርጋለሁ፤


ስለዚህ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ አወርዳለሁ፤ በኀይለኛ ቊጣዬም አጠፋቸዋለሁ፤ በደላቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ።” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ‘አንድ ነገር የማደርግበት ጊዜ ቀርቦአል፤ አልገታም፤ አልምርም፤ ሐሳቤን አለውጥም፤ እንደ አካሄድሽና እንደ ሥራሽ እፈርድብሻለሁ’ ” ብዬ ተናግሬአለሁ።


እስራኤላውያን ተማርከው የሄዱትም እኔን በመበደላቸው ምክንያት መሆኑን ሕዝቦች ሁሉ ያውቃሉ፤ እኔ ችላ ስላልኳቸው ጠላቶቻቸው በጦርነት ድል አድርገው ሁላቸውንም ገድለዋቸዋል።


እንደ ርኲሰታቸውና እንደ በደላቸው አደረግሁባቸው፤ ርዳታም አላደረግሁላቸውም።”


ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አሁን መጥፊያችሁ ደርሶአል። ቊጣዬን አወርድባችኋለሁ፤ እንደ አካሄዳችሁም እፈርድባችኋለሁ ስለ ርኲሰታችሁም ሁሉ እቀጣችኋለሁ።


“አሁን እኔ በቅርቡ ቊጣዬንና መዓቴን አወርድባችኋለሁ፤ እንዳካሄዳችሁም እፈርድባችኋለሁ፤ በአጸያፊ ድርጊታችሁም ምክንያት እቀጣችኋለሁ።


በአሕዛብ መካከል ትጠፋላችሁ፤ በጠላቶቻችሁም ምድር ተውጣችሁ ትቀራላችሁ።


“የእስራኤል ሕዝብ በሕዝቦች መካከል እንዲበተኑ አዛለሁ፤ የሚበተኑትም እህል በወንፊት እንደሚነፋ ዐይነት ነው፤ ነገር ግን ወንፊቱ ሲነቃነቅ ገለባው እንጂ አንድም ቅንጣት አይበተንም።


በርኲሰት ምክንያት አሠቃቂ ጥፋት የሚደርስ በመሆኑ በዚህ ማረፍ አይቻልም፤ ስለዚህ ተነሥታችሁ ሂዱ።


እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደየሥራው ይሰጠዋል።


“እግዚአብሔር በመላው ዓለም በሕዝቦች መካከል ከአንድ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ድረስ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ ሰግዳችሁላቸው የማታውቁትን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ባዕዳን አማልክት ታመልካለህ።


跟着我们:

广告


广告