Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 35:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ በሕዝቤ ላይ ባላችሁ ጥላቻ ምክንያት ያሳያችሁት ቊጣና ምቀኝነት ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እሰጣችኋለሁ። እነርሱም እናንተን በምቀጣበት ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከጥላቻችሁ የተነሣ በእነርሱ ላይ በገለጣችሁት ቍጣና ቅናት ልክ እፈርድባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ፣ ማንነቴ በእነርሱ መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱን ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቁጣህና እንደ ቅናትህ መጠን አደርጋለሁ፤ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ መካከል ማንነቴን አስታውቃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! እንደ ቍጣህ መጠን፥ እነ​ር​ሱ​ንም ጠል​ተህ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኸው እንደ ቅን​አ​ትህ መጠን እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በፈ​ረ​ድ​ሁ​ብ​ህም ጊዜ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና እንደ ቍጣህ መጠን እነርሱንም ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቅንዓትህ መጠን እኔ እሠራለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ ዘንድ የታወቅሁ እሆናለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 35:11
8 交叉引用  

እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤ “እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ መጮኻቸውንም አስታውስ።


እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።


ኤዶምን የምበቀላት በሕዝቤ በእስራኤል አማካይነት ነው፤ እስራኤላውያን በኤዶም ላይ እንደ ቊጣዬ ኀይለኛነት ይበቀላሉ፤ ኤዶማውያንም እኔ እንደ ተበቀልኳቸው ይረዳሉ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኤዶም ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ወንድሞቻቸውን እስራኤላውያንን በሰይፍ አሳደዋቸዋል፤ ከያዙአቸውም በኋላ ርኅራኄ አላደረጉላቸውም፤ በእነርሱ ላይ ያላቸው ቊጣ ሊበርድም አልቻለም፤


“እኔ እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ የምፈርድበት ቀን ደርሶአል፤ ኤዶም ሆይ! እንደ ሥራህ ዋጋህን ታገኛለህ፤ የምትፈጽመው ክፉ ሥራ በራስህ ላይ ይመለሳል።


በሌሎች ላይ በምትፈርዱበት ፍርድ፥ በእናንተም ላይ ይፈረድባችኋል፤ እንዲሁም በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።


የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።


跟着我们:

广告


广告