Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 35:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ ‘እኔ እግዚአብሔር እዚያ ያለሁ ብሆንም እንኳ ሁለቱን ሕዝቦች፥ ማለት ይሁዳንና እስራኤልን፥ እንዲሁም ምድራቸውን ጭምር የእናንተ አድርጋችሁ ለመውረስ አስባችሁ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ ‘እኔ እግዚአብሔር በዚያ እያለሁ፣ “እነዚህ ሁለት ሕዝቦችና ሁለት አገሮች የእኛ ይሆናሉ፤ እኛም እንወርሳቸዋለን።” ብለሃልና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታ በዚያ ሳለ፥ አንተ ግን፦ “እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦችና እነዚህ ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን” ብለሃልና፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፥ እነ​ዚህ ሁለቱ ሕዝ​ቦች፥ እነ​ዚ​ህም ሁለቱ ሀገ​ሮች ለእኔ ይሆ​ናሉ፤ እኔም እወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፦ እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች እነዚህም ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን ብለሃልና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 35:10
19 交叉引用  

እግዚአብሔር በይሁዳ የታወቀ ነው፤ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።


ስለዚህ አምላኬ ሆይ! እንደ ትቢያ፥ በነፋስም እንደሚወሰድ ገለባ በትናቸው።


በእናንተ መካከል ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ስለ ሆነ በጽዮን የምትኖሩ ሁሉ ‘እልል’ በሉ!”


ሽብር በተነሣ ጊዜ ምሽጋቸው ይፈርሳል፤ የጦር መኰንኖቻቸውም አርማቸውን ትተው በመርበድበድ ይሸሻሉ”። እሳቱ በጽዮን፥ እቶኑ በኢየሩሳሌም የሆነው እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


እግዚአብሔር ስለ ዐሞን እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትምን? ወራሾች የሉትምን? ታዲያ ሚልኮም የተባለውን ጣዖት የሚያመልኩ ወገኖች የጋድን ነገድ አስለቅቀው በከተሞቹ የሰፈሩት ለምንድን ነው?


“የሰው ልጅ ሆይ! በጢሮስ ከተማ ያሉ ሕዝቦች የሚደሰቱበት ነገር ይህ ነው፦ ‘ኢየሩሳሌም ፈራርሳለች! የንግድ ኀይልዋም ወድቋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከእኛ ጋር መወዳደር ከቶ ስለማትችል እኛ እንበለጽጋለን’ ይላሉ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ጠላቶች ‘እነሆ፥ እነዚያ የጥንት ተራራዎች የእኛ ሆነዋል!’ በማለት መጓደድ ጀምረዋል።


“በኀይለኛ ቅናቴ በሌሎች ሕዝቦች ላይና በመላዋ ኤዶም ላይ እናገራለሁ፤ እነርሱ ደስታን በተመላ ስሜትና በፍጹም ንቀት መሰማሪያዋን ለመውረር ምድሬን ርስታቸው አደረጉት፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


በአራቱም አቅጣጫ ያሉት የከተማይቱ የቅጽር ግንቦች ጠቅላላ ርዝመት ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ከአሁን በኋላ የከተማይቱ መጠሪያ ስም “እግዚአብሔር በዚያ አለ!” የሚል ይሆናል።


አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ የእኔ የሆኑትን ሕዝቤን እስራኤልን በሕዝቦች መካከል ስለ በታተኑና ምድሪቱን ስለ ተካፈሉ በኢዮሣፍጥ ሸለቆ ወደ ፍርድ አቀርባቸዋለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዐሞን ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ግዛት ለማስፋፋት ባደረጉት ወረራ በገለዓድ የሚኖሩትን እርጉዞች ሴቶች እንኳ ሆዳቸውን ቀደዋል።


ጠላቶቻቸው በሮቻቸውን ሰባብረው፥ ሀብታቸውን ሁሉ በዘረፉበት ቀን፥ አንተ በዳር ቆመህ ትመለከት ነበር፤ አንተ እኮ ኢየሩሳሌምን በዕጣ ከተከፋፈሉአት ሰዎች በምንም አትሻልም።


በችግራቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር ልትገባ ባልተገባህ ነበር፤ በመከራቸውም ቀን በይሁዳ ሕዝብ ጥፋት ለመደሰት መተባበር አይገባህም ነበር፤ በመጥፊያቸው ቀን የእነርሱን ንብረት መዝረፍ ባልተገባህም ነበር።


እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ያስተላለፈውን የቅጣት ፍርድ አንሥቶላችኋል፤ ጠላቶቻችሁንም አስወግዶላችኋል፤ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት ይደርስብናል ብላችሁ አትፈሩም።


እግዚአብሔር ራሱ በዙሪያዋ እንደ እሳት ቅጽር ሆኖ ከተማይቱን እንደሚጠብቅና በክብሩም በዚያ እንደሚኖር ተስፋ ሰጥቶአል።”


እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ስለ ሆንኩና በእናንተ በእስራኤል ሕዝብም መካከል ስለምኖር የእኔ መኖሪያ የሆነውንና እናንተ የምትኖሩበትን ምድር አታርክሱ።”


跟着我们:

广告


广告