Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 34:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 “በበጎች የተመሰላችሁትና እኔ የማሰማራችሁ መንጋ እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እናንተ በጎቼ የማሰማሪያዬ በጎች ያልኋችሁ፣ ሕዝብ ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እናንተም በጎቼ፥ የማሰማርያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ እኔም አምላካችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እና​ን​ተም በጎች፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እናንተም በጎቼ፥ የማሰማርያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ እኔም አምላካችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 34:31
16 交叉引用  

እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ የፈጠረን እርሱ ነው፤ እኛ የእርሱ ነን፤ ስለዚህ እኛ እንደ በጎች መንጋ የሚያሰማራን ሕዝቦቹ ነን።


ሕዝቡን አውጥቶ እንደ በጎች አሰማራቸው፤ በበረሓም እንደ በግ መንጋ መራቸው።


የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።


እርሱ አምላካችን ነው፤ እኛም እርሱ የሚጠነቀቅልን ሕዝቦቹና የሚያሰማራን መንጋዎቹ ነን፤ ስለዚህ ዛሬ እንዲህ ሲል የሚናገረውን አድምጡ፦


እንደ እረኛ ለመንጋው እንክብካቤ ያደርጋል፤ ግልገሎቹን በአንድነት ይሰበስባል፤ በእጆቹም ዐቅፎ ይወስዳቸዋል፤ እናቶቻቸውንም በርኅራኄ ይመራቸዋል።


“የእግዚአብሔር መንጋ የሆነውን ሕዝብ ለሚበትኑና ለሚያጠፉ መሪዎች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር፤


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


ቀድሞ ኢየሩሳሌም በበዓል ቀን ለመሥዋዕት በሚቀርቡ በጎች ትሞላ እንደ ነበረች የፈራረሱት ከተሞች በሕዝብ የተሞሉ ይሆናሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።


“እናንተ እንደ ታናናሽ መንጋ የሆናችሁ ወገኖቼ አትፍሩ፤ የሰማይ አባታችሁ መንግሥትን ሊሰጣችሁ ፈቅዶአል።


“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል።


በዚህ መንጋ ውስጥ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት ይገባኛል፤ እነርሱ ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ ይሆናል።


መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።


跟着我们:

广告


广告