Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 34:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ከዚያም በኋላ አሕዛብ አይመዘብሩአቸውም፤ አራዊትም ገድለው አይቦጫጭቁአቸውም፤ የሚያስፈራቸው ሳይኖር በሰላም ይኖራሉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከእንግዲህ ለሌሎች ሕዝቦች ንጥቂያ አይዳረጉም፤ የዱር አራዊት አይቦጫጭቋቸውም፤ ያለ ሥጋት ይኖራሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከእንግዲህም ለሕዝቦች ብዝበዛ አይሆኑም፥ የምድርም አራዊት አይበሉአቸውም፤ በሰላም ይኖራሉ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እን​ግ​ዲህ ለአ​ሕ​ዛብ ንጥ​ቂያ አይ​ሆ​ኑም፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት አይ​በ​ሉ​አ​ቸ​ዋም፤ ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጣሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እንግዲህም ለአሕዛብ ንጥቂያ አይሆኑም የምድርም አራዊት አይበሉአቸውም፥ ተዘልለውም ይቀመጣሉ የሚያስፈራቸውም የለም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 34:28
16 交叉引用  

ማንንም ሳትፈራ ትተኛለህ፤ ብዙ ሰዎችም በአንተ ፊት ሞገስ ማግኘትን ይፈልጋሉ።


የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከሐሳብና ከጭንቀት ነጻ ይሆናሉ፤ ቤቶቻቸውም በሰላምና በደኅንነት የተሞሉ ይሆናሉ።


የአገልጋዬ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ፥ አትፍሩ ተስፋም አትቊረጡ፤ ከሩቅ አገር በደኅና እመልሳችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ተማርከው ከተወሰዱበት አገር እመልሳቸዋለሁ፤ እስራኤላውያን እንደገና ሰላም አግኝተው ያለ ስጋት ይኖራሉ።


እንደ እሳት በሚነደው ታላቅ ቊጣዬ የበተንኳቸውን ሕዝብ ከተበተኑባቸው አገሮች ሁሉ እንደገና ወደዚህ ቦታ እሰበስባቸዋለሁ፤ በሰላም እንዲኖሩም አደርጋለሁ።


“የአገልጋዬ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አትፍሩ ተስፋም አትቊረጡ፤ እናንተን ከሩቅ አገር፥ ዘራችሁንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ። እናንተም እንደገና ማንም ሳያስፈራችሁ በሰላምና በደኅንነት ትኖራላችሁ።


የሰላም ዋስትና የሚያገኙበትን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ፤ አደገኞች የሆኑትን አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤ ስለዚህ በጎቼ በየመስኩ በሰላም ተሰማርተው ሊኖሩና በየጫካውም ሊያድሩ ይችላሉ።


ብዙ እህል የሚመረትበትን የእርሻ ቦታ አመቻችላቸዋለሁ፤ ዳግመኛ ለራብ አይጋለጡም፤ የሕዝቦች መሳለቂያም አይሆኑም።


በጎቹም እረኛ ስለሌላቸው ተበታተኑ፤ በመበታተናቸውም የምድር አራዊትም ቦጫጭቀው በሉአቸው።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እረኞቼ በጎቼን በመመገብና በመጠበቅ ፈንታ ራሳቸውን ብቻ ስለሚመግቡና የጠፉትን በጎቼን የሚፈልግና የሚጠብቅ እረኛ ስለሌላቸው የአውሬ ሲሳይ ሆነው ተበልተዋል።


ምድሪቱ ከእንግዲህ ወዲህ የሕዝቦች ማላገጫ አትሆንም፤ በንቀትም አይመለከቱአትም፤ ምድሪቱንም ዳግመኛ ልጅ አልባ የሚያደርጋት አይኖርም። እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ስለዚህ እናንተ የእስራኤል ተራራዎች የልዑል እግዚአብሔርን ቃል አድምጡ፦ ለተራሮችና ለኰረብቶች፥ ለወራጅ ውሃዎችና ለሸለቆዎች፥ ባድማና ወና ሆነው ለተለቀቁትና በአካባቢው ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የዘረፋ ምንጮችና የመሳለቂያ ርእስ ለሆኑት ከተሞች ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


የሚያስፈራቸው ነገር ሳይኖር በገዛ ምድራቸው በሰላም ይኖሩ በነበረ ጊዜ የፈጸሙትን አሳፋሪ ተግባርና ለእኔ አለመታመናቸውን ሁሉ ይረሳሉ።


እንደ ወፍ ከግብጽ፥ እንደ ርግብም ከአሦር እየበረሩ ይመጣሉ፤ ወደ መኖሪያቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ይህን የምናገር እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።”


ሕዝቤን እስራኤልን በሰጠኋቸው ምድር ላይ እተክላቸዋለሁ፤ ዳግመኛም ከዚያ ተነቅለው አይወጡም፤” ይህን የሚናገር እግዚአብሔር አምላካችሁ ነው።


ከምርኮ የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ በማንም ላይ ክፉ ነገር አያደርጉም፤ ሐሰት አይናገሩም፤ በአንደበታቸውም አያታልሉም፤ ስለዚህም ተመግበው በሰላም ይኖራሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።”


እህላቸውን በሰላም ዘርተው ፍሬውን ይሰበስባሉ የወይን ተክሎቻቸውም ያፈራሉ። በቂ ዝናብ ስለሚዘንብ ምድሪቱ ብዙ ሰብል ትሰጣለች፤ ከስደት ለተረፉት ሕዝብ ይህን ሁሉ በረከት እሰጣለሁ።


跟着我们:

广告


广告