Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 34:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔ ልዑል እግዚአብሔር የበጎቹን እረኞች እቃወማለሁ፤ በጎቹን ከእረኞች እጅ ወስጄ እንዳያሰማሩአቸው አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እረኞቹ ራሳቸውን አይመግቡም፤ ለእነርሱም ምግብ እንዳይሆኑ በጎቼን ከእነርሱ አፍ አስጥላለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ በእረኞች ላይ ተነሥቻለሁ፤ ስለ መንጋዬ እጠይቃቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ እረኞች ራሳቸውን መመገብ እንዳይችሉ፣ መንጋዬን እንዳያሰማሩ አደርጋለሁ። መንጋዬን ከአፋቸው አስጥላለሁ፤ ከእንግዲህም ምግብ አይሆናቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በእረኞች ላይ ነኝ፥ መንጋዎቼን ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ መንጋዎቼን ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያስማሩም፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በእ​ረ​ኞች ላይ ነኝ፤ በጎ​ች​ንም ከእ​ጃ​ቸው እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በጎ​ች​ንም ከማ​ሰ​ማ​ራት አስ​ተ​ዋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ወዲያ እረ​ኞች በጎ​ችን አያ​ሰ​ማ​ሩም፤ በጎ​ች​ንም ከአ​ፋ​ቸው አድ​ና​ለሁ፤ መብ​ልም አይ​ሆ​ኑ​ላ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያስማሩም፥ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 34:10
26 交叉引用  

በጠላቶቼ ፊት ታላቅ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ትቀባልኛለህ፤ ጽዋዬም እስኪትረፈረፍ ድረስ ይሞላል።


አንቺም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በሜዳ ላይ እንደሚገኝ ቋጥኝ ከሸለቆዎች በላይ ከፍ ብለሽ ትታዪአለሽ፤ ነገር ግን እኔ እዋጋሻለሁ፤ አንቺ ግን ማንም የሚደፍርሽና ምሽጎችሽን ጥሶ የሚገባ ያለ አይመስልሽም፤


ይኸውም በሪብላ ንጉሥ ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ልጆቹ እንዲገደሉ ተደረገ፤ የይሁዳ ባለሥልጣኖችም ሁሉ ሞት ተፈረደባቸው።


“ትዕቢተኛይቱ ባቢሎን ሆይ! እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በአንቺ ላይ እነሣለሁ፤ አንቺንም የምቀጣበት ጊዜ ደርሶአል።


ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ሐሰተኛ ራእይ አታዩም፤ የሟርተኝነትንም ሥራ አትሠሩም፤ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦ “ሐሰትን ስለ ተናገራችሁና ራእያችሁም ውሸት ስለ ሆነ እኔ በእናንተ ላይ እነሣለሁ። ይህንን የተናገርኩ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ነኝ።


እንዲህም በላት! ‘እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ ሰይፉን ከሰገባው አውጥቼ ኃጢአተኛውንና ጻድቁን ከመካከልሽ አጠፋለሁ።


እኔ አንድን በደለኛ በኃጢአቱ ምክንያት በእርግጥ ትሞታለህ ብለው አንተ ግን ያን ሰው ከኃጢአቱ ተመልሶ ይድን ዘንድ ባታስጠነቅቀው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል፤ ስለ እርሱ ሞት ግን አንተን ተጠያቂ አደርግሃለሁ።


“በደግነቱ የታወቀ ጻድቅ ሰው ክፉ ሥራ መሥራት ቢጀምርና እኔም በችግር ላይ እንዲወድቅ ባደርገው፥ አንተ ካላስጠነቀቅኸው በቀር በኃጢአቱ ይሞታል፤ ከዚያ በፊት የፈጸመው መልካም ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ስለ እርሱ ሞት አንተን በኀላፊነት እጠይቅሃለሁ።


“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ጠባቂዎች ላይ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን ሁሉ በትንቢት እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘መንጋውን መንከባከብና መጠበቅ ትታችሁ ራሳችሁን የምትጠብቁ እናንተ የእስራኤል እረኞች ወዮላችሁ!


ነገር ግን እኔ በጎቼን እታደጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ዘርፎ እንዲወስዳቸው አልፈቅድም፤ በመልካም በግና በክፉ በግ መካከል እፈርዳለሁ፤


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እረኞቼ በጎቼን በመመገብና በመጠበቅ ፈንታ ራሳቸውን ብቻ ስለሚመግቡና የጠፉትን በጎቼን የሚፈልግና የሚጠብቅ እረኛ ስለሌላቸው የአውሬ ሲሳይ ሆነው ተበልተዋል።


ስለዚህም እናንተ እረኞች አድምጡኝ።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኤዶም ሕዝብ ሆይ! እነሆ እኔ እናንተን እቃወማለሁ፤ ምድራችሁንም ባድማና ወና ላደርግ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ።


በዚህም ምክንያት እኔ ልዑል እግዚአብሔር በአንቺ በኢየሩሳሌም ላይ በቊጣ የተነሣሁብሽ መሆኔን እገልጥልሻለሁ፤ ሕዝቦች ሁሉ እያዩ በፍርድ እቀጣሻለሁ።


ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኀይለኛ ቊጣዬ በሕዝቤ መሪዎች ላይ ይወርዳል፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ለመንጋዬ ለይሁዳ ሕዝብ ስለምጠነቀቅ መሪዎቻቸውን እቀጣለሁ፤ የይሁዳንም ሕዝብ እንደ ኲሩ የጦር ፈረሴ አደርጋቸዋለሁ።


ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ በሥልጣናቸውም ሥር ሁኑ፤ እነርሱ የሚጠየቁበት ኀላፊነት ስላለባቸው ስለ ነፍሳችሁ ጉዳይ ይተጋሉ፤ እናንተ ብትታዘዙአቸው እነርሱ ሥራቸውን በደስታ ያከናውናሉ፤ ያለበለዚያ ሥራቸውን በሐዘን ይሠራሉ፤ ይህም እናንተን የሚጠቅም አይሆንም።


የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ይመለከታሉ፤ ጆሮዎቹም ጸሎታቸውን ለመስማት ተከፍተዋል፤ በክፉ አድራጊዎች ላይ ግን ጌታ የቊጣ ፊቱን ያሳያል።”


跟着我们:

广告


广告