Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኃጢአተኛውን ሰው ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ካስጠነቀቅኸው በኋላ፥ ከክፉ ሥራው ሳይመለስ በኃጢአቱ ጸንቶ ቢሞት ግን፥ አንተ ራስህን ከኀላፊነት ነጻ ታደርጋለህ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነገር ግን ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ አስጠንቅቀኸው ከመንገዱ ባይመለስ፣ እርሱ ስለ ኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ራስህን አድነሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ሰው ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን ከመ​ን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብታ​ስ​ጠ​ነ​ቅ​ቀው፥ እር​ሱም ከመ​ን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:9
24 交叉引用  

ትክክለኛውን መንገድ ትቶ ስሕተት የሆነ ነገር የሚያደርግ ይቀጣል፤ ተግሣጽንም የሚጠላ ይጠፋል።


ብዙ ጊዜ ተገሥጾ በእምቢተኛነቱ የሚጸና ሰው በድንገት ይሰበራል። ፈውስም አይኖረውም።


ኃጢአተኛውን አስጠንቅቀኸው፥ ከኃጢአቱ ባይመለስ እርሱ በኃጢአተኛነቱ ይሞታል፤ አንተም በኀላፊነት ከመጠየቅ ራስህን ታድናለህ።


በደግነቱ የታወቀ ጻድቅ ሰው ኃጢአት ከመሥራት እንዲገታ ብታስጠነቅቀውና የአንተን ማስጠንቀቂያ ተቀብሎ ኃጢአት ከመሥራት ቢቈጠብ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ አንተም በኀላፊነት ከመጠየቅ ራስህን ታድናለህ።”


ጠባቂውም ጠላት ሲመጣ ቢያይና ከአደጋ መጠንቀቅ የሚያስችል የመለከት ድምፅ ለሰዎች ሁሉ ቢያሰማ፥


ማንም ሰው ይህን የማስጠንቀቂያ ድምፅ ሰምቶ ባለማጤኑ ምክንያት ጠላት አደጋ ጥሎበት ቢሞት ጥፋቱ የራሱ ነው፤


ነገር ግን ጠባቂው ጠላት ሲመጣ እያየ ከአደጋ ማስጠንቀቂያውን ድምፅ ሳያሰማ ቢቀር፥ ጠላት መጥቶ ከእነዚያ መካከል አንዱን ቢገድል ያ ሰው የሞተው በኀጢአቱ ነው፤ እኔ ግን ስለ እርሱ ለደሙ ኀላፊ አድርጌ የምጠይቀው ጠባቂውን ነው።’


“የጌታውን ፈቃድ እያወቀ ያልተዘጋጀ፥ ወይም የጌታውን ትእዛዝ ያልፈጸመ አገልጋይ በብርቱ ይቀጣል።


የእኔን ማንነት ዐውቃችሁ ባታምኑ ከእነኃጢአታችሁ የምትሞቱ ስለ ሆነ ከነኀጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኳችሁ ስለዚህ ነው።”


ስለዚህ በነቢያት እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤


‘እናንተ ፌዘኞች እዩ! ተደነቁ! ጥፉም! ማንም ሰው ቢያወራላችሁ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እሠራለሁ።’ ”


ጳውሎስና በርናባስ ግን እንዲህ ሲሉ በድፍረት ተናገሩ፤ “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ እንዲነገር አስፈላጊ ነው፤ እናንተ አንቀበልም ካላችሁና የዘለዓለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን እነሆ፥ እኛ ዞር ብለን ወደ አሕዛብ እንሄዳለን።


ስለዚህ ከእናንተ አንድ እንኳ ቢጠፋ ኀላፊነት እንደሌለብኝ በዛሬው ቀን አስገነዝባችኋለሁ።


ወንድሞች ሆይ! “ሰነፎችን ገሥጹ፤ ፈሪዎችን አደፋፍሩ፤ ደካሞችን እርዱ፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ” ብለን እንመክራችኋለን።


ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!


ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


跟着我们:

广告


广告