Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ሥጋ ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ጣዖት ታመልካላችሁ፤ ግድያ ትፈጽማላችሁ፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ እንዴት ምድሪቱ የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዐይኖቻችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምም ታፈስሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ታስባላችሁ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፥ ዓይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፥ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም ወደ ጣዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ታነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ደም​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፥ ዓይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፥ ደምንም ታፈስሳላችሁ፥ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:25
29 交叉引用  

ነገር ግን በደሙ ውስጥ ሕይወት ስላለ ደም ያለበትን ሥጋ አትብሉ።


ይህን ማድረግ የሚችል፥ እጆቹ ከክፉ ሥራና ልቡም ከክፉ ሐሳብ ንጹሓን የሆኑ፥ ጣዖትን የማያመልክ፥ ዋሽቶ የማይምል ነው።


ወንድሞቻችሁ የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ እንዳሳደድኩ፥ እናንተንም ከፊቴ አሳድዳችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


“እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፦ ‘በመሠዊያችሁ ላይ የምታቀርቡትን የሚቃጠለውንም ሆነ ሌላውን መሥዋዕታችሁን ሰብስባችሁ ሥጋውን ለራሳችሁ ብሉት።’


ድኾችንና ችግረኞችን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማ፥ ገንዘብ ሲያበድር በመያዣ ስም የወሰደውን ቢያስቀር፥ በአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች ጣዖትን ቢያመልክ አጸያፊ ነገሮችን ቢያደርግ፥


ለእስራኤላውያን ጣዖቶች ባይሰግድ፥ ወይም በተከለከሉ መስገጃዎች የተሠዋውን ማንኛውንም ነገር ባይመገብ፥ የሌላ ሰው ሚስት ባይደፍር፥


ለእስራኤላውያን ጣዖቶች አይሰግድም፤ ወይም በተከለከሉ መስገጃዎች የተሠዋውን ማንኛውንም ነገር አይመገብም፤ የሌላ ሰው ሚስትን አይደፍርም፤ ወይም የወር አበባ ከታያት ሴት ጋር ግንኙነት አያደርግም፤


ባለ ሥልጣኖቹ፥ የገደሉትን እንስሳ እንደሚቦጫጭቁ ተኲላዎች ናቸው፤ ያለ አግባብ ለመበልጸግ ሰውን ይገድላሉ፤


ለከተማይቱ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ በውስጥሽ ያሉትን ብዙዎችን ስለ ገደልሽና ጣዖቶችን በማምለክ ራስሽን ስላረከስሽ እንድትጠፊ የተወሰነበት ጊዜ ተቃርቦአል።


በውስጥሽ ያሉ የእስራኤል መሪዎች ሁሉ እንደየ ሥልጣናቸው የግድያ ወንጀል ይፈጽማሉ፤


ከእናንተ አንዳንዶቹ ሌሎችን ለማስገደል ሐሰት ይናገራሉ፤ አንዳንዶቹ ለጣዖት የተሠዋውን ሁሉ ይመገባሉ፤ አንዳንዶቹ ዘወትር ፍትወታቸውን ለማርካት ይጣደፋሉ።


በሀገሪቱ ላይ ስለ ፈጸሙት ግድያና በጣዖት አምልኮም ምድሪቱን በማርከሳቸው ምክንያት ኀይለኛ ቊጣዬን አወረድኩባቸው።


እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ እጅግ የከፋ ኃጢአት በመሥራት በድለዋል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ግድያ ፈጽመዋል፤ ከተማይቱንም በዐመፅ የተሞላች አድርገዋታል፤ ‘እግዚአብሔር አገራችንን ትቶአታል፤ እኛንም አይመለከተንም’ ይላሉ፤


“ደም ያለበትን ሥጋ አትብሉ፤ የአስማትን ነገር አትከተሉ፤


ከእስራኤላውያን ወገን ስብ የሆነውን ሥጋ ወይም የእንስሶችን ደም የሚመገብ አይኑር፤ ይህም እስራኤላውያን በሚኖሩበት ዘመንና ቦታ ሁሉ ለዘለዓለሙ ተጠብቆ የሚኖር ቋሚ ሥርዓት ይሁን።


ነገር ግን አንድ ሰው ንጹሕ ሳይሆን የአንድነቱን መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ከእግዚአብሔር ሕዝብ መለየት አለበት፤


ማንም ሰው ንጹሕ ያልሆነው ከሰው ወይም ከእንስሶች የሚወጣ ማንኛውንም ርኩስ ነገር ነክቶ ይህን የአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይለይ። ”


ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ብትጠበቁ መልካም ታደርጋላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”


ከአሕዛብ ወገን ያመኑት ግን ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ’ የሚለውን ውሳኔ የያዘ ደብዳቤ ጽፈን ልከንላቸዋል።”


ነገር ግን ደማቸውን አትብላ፤ ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው፤


ነገር ግን የሕይወት መኖሪያ በደም ውስጥ ስለ ሆነ ደም ያለበትን ሥጋ ከመብላት ብቻ ተጠንቀቅ፤ ስለዚህ ሕይወትን ከሥጋ ጋር አትብላ።


ደማቸውን እንደ ምግብ አድርጋችሁ አትመገቡት፤ ነገር ግን ደሙን እንደ ውሃ በምድር ላይ አፍስሱት።


በሰማይ ላይ የምታዩአቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ወይም የሰማይን ሠራዊት ሁሉ በማምለክና ለእነርሱ በመስገድ እንዳትፈተኑ ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን ሁሉ ሌሎች ሕዝቦች ብቻ ያመልኩአቸው ዘንድ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።


跟着我们:

广告


广告