Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ምድር በፈራረሱ ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ ‘አብርሃም ብቸኛ የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤ ምድሪቱ በሞላ ለእርሱ ተሰጠች፤ እኛ ግን እነሆ፥ ብዙዎች ነን፤ ምድሪቱም በእርግጥ በርስትነት ተሰጥታናለች።’

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል ምድር በፍርስራሾች ውስጥ የሚኖሩት ሕዝቦች፣ ‘አብርሃም አንድ ራሱን ብቻ ነበር፤ ያም ሆኖ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛ ግን ብዙዎች ነን፤ በርግጥ ምድሪቱ ርስት ሆና ተሰጥታናለች’ ይላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር ባሉ ፍርስራሽ ስፍራዎች የሚኖሩ፦ አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛ ደግሞ ብዙዎች ነን ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች ይላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር በአሉ በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች የተ​ቀ​መጡ፦ አብ​ር​ሃም ብቻ​ውን ሳለ ምድ​ሪ​ቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙ​ዎች ነን፤ ምድ​ሪ​ቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች ይላሉ። ስለ​ዚህ እን​ዲህ በላ​ቸው፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር ባሉ በባድማ ስፍራዎች የተቀመጡ፦ አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ፥ እኛም ብዙዎች ነን ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች ይላሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:24
21 交叉引用  

አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”


እርሱም ለአንተ ታማኝ እንደ ሆነ ተመልክተህ፥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳንን አደረግህ፤ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ኢያቡሳውያንና ጌርጌሳውያን የሚኖሩባትንም የከነዓንን ምድር ለዘሮቹ መኖሪያ ርስት አድርገህ ልትሰጠው ቃል ገባህለት፤ አንተ ታማኝ ስለ ሆንክ ቃል ኪዳንህን አጽንተህ ጠብቀሃል።


ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃምና ወደ ወለደቻችሁ ወደ ሣራ ተመልከቱ፤ አብርሃምን በጠራሁት ጊዜ ልጅ አልነበረውም፤ ነገር ግን እኔ ባረክሁት፤ ዘሩንም አበዛሁለት።


ምንም ሀብት ያልነበራቸውን ድኾች ብቻ በይሁዳ ምድር ተወ፤ ለእነርሱም የወይን ተክል ቦታዎችንና የሚያርሱት መሬት ሰጣቸው።


ከይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች ጥቂቶቹ ገና እጃቸውን አልሰጡም ነበር፤ እነርሱም የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን በሀገሪቱ ላይ ገዢ አድርጎ እንደ ሾመውና ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ በሀገሪቱ ለቀሩት ድኾች ኀላፊ ያደረገው መሆኑን ሰሙ፤


እነዚያም ሰዎች ከተማይቱ ውስጥ እንደ ገቡ የናታልያ ልጅ እስማኤልና ተከታዮቹ ገድለው ጒድጓድ ውስጥ ጣሉአቸው።


“የሰው ልጅ ሆይ! የኢየሩሳሌም ኗሪዎች ስለ ሥጋ ዘመዶችህ፥ ስለ ተሰደዱት ወገኖችህ፥ በአጠቃላይ ስለ መላው የእስራኤል ሕዝብ በመነጋገር ላይ ናቸው፤ ‘እነርሱ ከእግዚአብሔር ርቀው ስለ ሄዱ እግዚአብሔር ምድሪቱን ለእኛ ርስት አድርጎ ሰጥቶናል’ ይላሉ”።


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


“እንግዲህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ በፈራረሱ ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ በእርግጥ ይገደላሉ ብዬ ያስጠነቀቅኋቸው መሆኑን ገልጠህ ንገራቸው፤ በገጠር የሚኖሩ የአራዊት ምግብ ይሆናሉ፤ በየተራራውና በየዋሻው ተደብቀው ያሉትም በመቅሠፍት ያልቃሉ፤


“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ጠባቂዎች ላይ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን ሁሉ በትንቢት እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘መንጋውን መንከባከብና መጠበቅ ትታችሁ ራሳችሁን የምትጠብቁ እናንተ የእስራኤል እረኞች ወዮላችሁ!


ስለዚህ እናንተ የእስራኤል ተራራዎች የልዑል እግዚአብሔርን ቃል አድምጡ፦ ለተራሮችና ለኰረብቶች፥ ለወራጅ ውሃዎችና ለሸለቆዎች፥ ባድማና ወና ሆነው ለተለቀቁትና በአካባቢው ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የዘረፋ ምንጮችና የመሳለቂያ ርእስ ለሆኑት ከተሞች ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።


‘እኛ የአብርሃም ልጆች ነን’ በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ።


ይልቁንስ ንስሓ መግባታችሁን የሚያመለክት ሥራ ሥሩ እንጂ እኛ የአብርሃም ልጆች ነን እያላችሁ በልባችሁ አትመኩ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።


እነርሱ ግን “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ከቶ ለማንም ባሪያ ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ፥ አንተ ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ የምትለን እንዴት ነው?” አሉት።


እነርሱም “አባታችን አብርሃም ነው” ሲሉ መለሱለት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር፤


ይሁን እንጂ የእግር ማሳረፊያ እንኳ የሚያኽል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ይህችን አገር ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ እንደሚሰጠው ቃል ገብቶለት ነበር፤ ይህን ቃል የገባለትም አብርሃም ገና ልጅ ሳይኖረው ነበር።


እንዲሁም አብርሃም ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት አባት የሆነበትም ምክንያት በመገረዛቸው ብቻ ሳይሆን እርሱ ከመገረዙ በፊት የነበረውን እምነት በመከተላቸውም ጭምር ነው።


እንዲሁም የአብርሃም ዘር ሁሉ የአብርሃም ልጆች ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር አብርሃምን “ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ ነው” ስላለው ነው፤


ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።


跟着我们:

广告


广告