Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አምልጦ የመጣው ሰው እኔ ዘንድ ከመድረሱ ከአንድ ቀን በፊት በምሽቱ የእግዚአብሔር ኀይል ወደ እኔ መጣ፤ በማግስቱ ጠዋት ሰውዬው ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት እግዚአብሔር አንደበቴን ከፈተልኝ፤ ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መናገር አልተሳነኝም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሰውየው ከመድረሱ በፊት በነበረው ምሽት፣ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ላይ ነበረች፤ በማለዳም ሰውየው ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ፤ ከዚያ በኋላ ዝም አላልሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ያመ​ለ​ጠ​ውም ሳይ​መጣ በመሸ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ በነ​ጋ​ውም ወደ እኔ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከ​ፈ​ተች፤ ከዚ​ያም በኋላ እኔ ዲዳ አል​ሆ​ን​ሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ያመለጠውም ሳይመጣ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፥ አፌም ተከፈተች ከዚያም በኋላ እኔ ዲዳ አልሆንሁም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:22
12 交叉引用  

በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የእግዚአብሔር ቃል የቡዚ ልጅ ወደ ሆንኩት ወደ ካህኑ ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ ነበረ።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! ዘወትር ሊያዩትና ሊጐበኙት የሚወዱትን፥ የሚመኩበትንና የሚደሰቱበትን እጅግ ጽኑ የሆነውን ቤተ መቅደስ ከእነርሱ እወስድባቸዋለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም እወስዳለሁ።


“ይህ በሚሆንበት ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ አበረታለሁ፤ አንተም ሕዝቅኤል ሆይ! ሰዎች ሊያደምጡህ በሚችሉበት ቦታ ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ እንድትናገር አደርግሃለሁ፤ በዚህም ሁኔታ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ኀይል በእኔ ላይ ነበረ፤ “ተነሥተህ ወደ ሸለቆ ሂድ፤ በዚያም አነጋግርሃለሁ” አለኝ።


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


የእግዚአብሔር ኀይል በእኔ ላይ መጣ፤ የእርሱም መንፈስ እኔን ወስዶ ብዙ አጥንቶች በተከማቸበት ሸለቆ ውስጥ አኖረኝ፤


በተሰደድን በሃያ አምስተኛው ዓመት፥ ኢየሩሳሌምም በጠላት እጅ በወደቀች በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ በመጀመሪያው ወር፥ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፥ በዚያው ዕለት የእግዚአብሔር ኀይል ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ እርሱም ብድግ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደኝ፤


በተሰደድን በስድስተኛው ዓመት፥ በስድስተኛው ወር፥ በአምስተኛው ቀን፥ ከይሁዳ የተሰደዱት ሕዝብ መሪዎች በቤቴ ከእኔ ጋር አብረው ተቀምጠው ሳሉ፥ የልዑል እግዚአብሔር ኀይል ድንገት በእኔ ላይ ወረደ።


በዚያኑ ጊዜ ዘካርያስ አንደበቱ ተፈቶለት መናገር ቻለ፤ እግዚአብሔርንም ማመስገን ጀመረ።


እናንተ በቆሮንቶስ የምትኖሩ ሰዎች ሆይ! እነሆ፥ በግልጥ ተናግረናችኋል፤ ልባችንንም በሰፊው ከፍተንላችኋል።


跟着我们:

广告


广告