Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በተሰደድን በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፥ ዐሥረኛው ወር በገባ በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም አምልጦ የመጣ አንድ ሰው ከተማይቱ በጠላት እጅ መውደቋን ነገረኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በተማረክን በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፣ በዐሥረኛው ወር፣ በዐምስተኛው ቀን፣ ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፣ “ከተማዪቱ ወደቀች!” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እንዲህም ሆነ፥ በተማረክን በዓሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተማይቱ ተመታች አለኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በተ​ማ​ረ​ክን በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተ​ማ​ዪቱ ተያ​ዘች አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እንዲህም ሆነ፥ በተማረክን በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተማይቱ ተመታች አለኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:21
15 交叉引用  

በክብር ዘቡ አዛዥ ሥር የነበሩት የባቢሎናውያን ወታደሮች የኢየሩሳሌም ዙሪያ አጥር


የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።


የክብር ዘብ አዛዡ ናቡዛርዳን እኔን በራማ ነጻ ከለቀቀኝ በኋላ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤ ከዚያ በፊት እኔ እዚያ የተወሰድኩት አሁን ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ በመማረክ ታስረው ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ሕዝብ ሁሉ ጋር በሰንሰለት ታስሬ ነበር።


ይህም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ኢኮንያን ከተማረከ አምስት ዓመት ከአምስት ቀን ሆኖት ነበር፤


በተሰደድን በዘጠነኛው ዓመት፥ በዐሥረኛው ወር፥ በዐሥረኛው ቀን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ኢየሩሳሌምን መክበብ የሚጀምርበት ስለ ሆነ ይህን የዛሬውን ዕለት በመዝገብ ጻፈው፤


በተሰደድን በዐሥራ አንደኛው ዓመት፥ ሦስተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


በተሰደድን በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፥ ዐሥራ ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


በተሰደድን በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


በተሰደድን በሃያ አምስተኛው ዓመት፥ ኢየሩሳሌምም በጠላት እጅ በወደቀች በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ በመጀመሪያው ወር፥ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፥ በዚያው ዕለት የእግዚአብሔር ኀይል ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ እርሱም ብድግ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደኝ፤


跟着我们:

广告


广告