Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ለሕዝብህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በአንድ አገር ላይ ጦርነትን ባመጣ ሕዝቡም በመካከሉ ጠባቂ ቢመድብ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለአገርህ ሰዎች ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘በምድር ላይ ሰይፍን ሳመጣ፣ የምድሪቱ ሕዝብ ከሰዎቻቸው አንዱን መርጠው ጕበኛ ቢያደርጉት፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ለሕዝብህ ልጆች ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፦ ሰይፍን በምድር ላይ ባመጣሁ ጊዜ፥ የምድሪቱ ሕዝብ ከመካከላቸው አንድ ሰው ወስደው ለራሳቸው ዘበኛ ያደርጉታል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ለሕ​ዝ​ብህ ልጆች ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጦርን በም​ድር ላይ በአ​መ​ጣሁ ጊዜ፥ የም​ድር ሕዝብ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አንድ ሰውን ወስ​ደው ለራ​ሳ​ቸው ጕበኛ ቢያ​ደ​ርጉ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ለሕዝብ ልጆች ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ሰይፍን በምድር ላይ ባመጣሁ ጊዜ፥ የምድር ሕዝብ ከመካከላቸው ሰውን ወስደው ለራሳቸው ጕበኛ ቢያደርጉ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:2
26 交叉引用  

ኢየሩሳሌም ሆይ! በቅጥሮችሽ ላይ ቀንና ሌሊት ዝም የማይሉ ጠባቂዎችን አኑሬአለሁ፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምትለምኑ ዕረፍት አታድርጉ።


በረሓማ ከሆነው ከባዶ ተራራ አጥፊዎች ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ሀገሪቱን ከዳር እስከ ዳር ስለሚያጠፋ አንድም ሰው አይድንም።


እግዚአብሔር ሕዝቡን በሚገሥጽበት ጊዜ የሚያሰማው ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል፤ በሕዝቦች ሁሉ ላይ ይፈርዳል፤ ክፉዎችንም በሞት ይቀጣል፤’ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።”


በባቢሎን ቅጥር ላይ አደጋ ጣሉ የሚል ምልክት አሳዩ! ጥበቃውን አጠናክሩ! ሰላዮችን መድቡ! ደፈጣ ተዋጊዎችንም አዘጋጁ፤ ይህንንም የምታደርጉት እግዚአብሔር በባቢሎን ሕዝብ ላይ ያቀደውንና የተናገረውን ተግባራዊ ስለሚያደርግ ነው።


እናንተ ጦርነትን ፈርታችኋል፤ እኔ ግን ጦርነትን አመጣባችኋለሁ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


“ወይም በዚያች አገር ጦርነትን አምጥቼ ሰዎችና እንስሶች በአጥፊ መሣሪያ እንዲወድሙ ባደርግ፥


ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ሕዝብንና እንስሶችን በአንድነት ለመጨረስ ጦርነትን፥ ራብን፥ አራዊትንና ቸነፈርን እነዚህን እጅግ የከፉ አራት መቅሠፍቶች በኢየሩሳሌም ላይ አመጣለሁ።


በምርኮ ወደሚገኙት የአገርህ ሕዝብ ሄደህ ቢሰሙህም ባይሰሙህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምላቸውን ሁሉ ንገራቸው።”


ዳግመኛ ስናገርህና አንደበትህን ስከፍትልህ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ “ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እነርሱ ዐመፀኞች ስለ ሆኑ ለመስማት የሚፈቅዱ ይስሙ፥ ለመስማት የማይፈቅዱ ይተዉት።’ ”


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! ጻድቅ የነበረ ሰው ኃጢአት መሥራትን ቢጀምር፥ ቀድሞ የፈጸመው መልካም ሥራ አያድነውም፤ ክፉ ሰውም ክፉ መሥራቱን ካቆመ የቀድሞ ክፉ ሥራው እንቅፋት አይሆንበትም፤ ጻድቅ ሰውም ኃጢአት መሥራት ቢጀምር፥ የቀድሞ ጽድቁ ከሞት ሊያድነው አይችልም።


“የአንተ ሕዝብ ግን እኔ የማደርገው ነገር ትክክል አይደለም ይላሉ፤ ይልቅስ ትክክል ያልሆነው የእነርሱ መንገድ ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ሕዝቡ በከተማይቱ ቅጽር አጠገብና በየቤታቸው ደጃፍ የሚወያዩት ስለ አንተ ነው፤ እርስ በርሳቸውም ‘ኑና ከእግዚአብሔር ምን ቃል እንደ መጣ ሲነገር እንስማ’ ይላሉ።


“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ፥ እኔ አንተን ለእስራኤል ሕዝብ ጠባቂ አድርጌሃለሁ፤ እኔ የምሰጥህን ማስጠንቀቂያ ሁሉ ለእነርሱ ማስተላለፍ አለብህ፤


ሕዝብህም ይህ ምን መሆኑን እንድትነግራቸው በሚጠይቁህ ጊዜ፥


የእስራኤል ተራራዎች የልዑል እግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ ንገራቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምናገረውን ተራራዎች፥ ኮረብቶችንና ገደላማ ሸለቆዎች ሁሉ ይስሙ፤ ሕዝቦች ለጣዖቶች የሚሰግዱባቸውን ከፍተኛ ቦታዎች ሁሉ የሚያጠፋ ሰይፍ እልካለሁ።


እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ነቢዩ ጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል፤ ሆኖም በመንገዱ ሁሉ ወጥመድ ተዘርግቶበታል፤ በአምላኩም ቤተ መቅደስ ጥላቻ ይጠብቀዋል።


ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን በማፍረሳችሁ እናንተን ለመቅጣት ጦርነት አመጣባችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ብትሰበሰቡም ሊፈወስ የማይችል በሽታ በመካከላችሁ እልካለሁ፤ ለጠላቶቻችሁም እጃችሁን ለመስጠት ትገደዳላችሁ።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።


跟着我们:

广告


广告