Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አንድን ክፉ ሰው በእርግጥ እንደሚሞት ባስታውቀውና እርሱ ግን ኃጢአት መሥራቱን ትቶ ሕጋዊና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ቢያደርግ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንዲሁም ክፉውን ሰው፣ ‘በርግጥ ትሞታለህ’ ብለው፣ እርሱም ከኀጢአቱ ተመልሶ ቀናውንና ትክክለኛውን ነገር ቢያደርግ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እኔም ኃጢአተኛውን ሰው፦ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ እርሱ ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኔም ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን ቢያ​ደ​ርግ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እኔም ኃጢአተኛውን፦ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:14
17 交叉引用  

ኃጢአቱን የሚደብቅ ኑሮው አይሳካለትም፤ ኃጢአቱን ተናዝዞ ዳግመኛ ኃጢአት ከመሥራት የሚቈጠብ ግን የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኛል።


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


ክፉዎች አካሄዳቸውን፥ ኃጢአተኞች ክፉ ሐሳባቸውን ይተዉ፤ ምሕረቱ ብዙ ስለ ሆነ ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ እኔ ለመመለስ ከፈለጋችሁ እነዚያን አጸያፊ ጣዖቶችን አስወግዳችሁ ለእኔ ብቻ ታማኞች ብትሆኑ፥


“እኔ ተስፋ ያላስቈረጥኳቸውን ጻድቃንን ሐሰት በመናገር ተስፋ አስቈርጣችኋል፤ ክፉዎች ሕይወታቸውን ለማዳን ከኃጢአታቸው እንዳይመለሱ አደፋፍራችኋል።


“ክፉ ሰው ኃጢአት መሥራትን ትቶ ሕጌን ቢጠብቅ፥ ትክክልና መልካም የሆነውን ነገር ቢያደርግ፥ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም፤


እንዲሁም ክፉ ሰው ኃጢአት መሥራት ትቶ ፍትሓዊና ትክክለኛ ሥራ ቢሠራ ሕይወቱን ያድናል፤


ክፉም ሰው ኃጢአት መሥራትን ትቶ እውነተኛና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ቢያደርግ በእርሱ ይኖራል።


ኃጢአተኛውን ሰው ‘ኃጢአተኛ ሆይ! በእርግጥ ትሞታለህ’ በምለው ጊዜ አንተ ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ባታስጠነቅቀው፥ ያ ሰው ኃጢአተኛ እንደ ሆነ በኃጢአቱ ይሞታል፤ ስለ እርሱም ሞት አንተን ራስህን በኀላፊነት ተጠያቂ አደርግሃለሁ።


የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በኃጢአታችሁ ምክንያት የተሰናከላችሁ ስለ ሆነ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የሕዝቤን አለመታመን ፈውሼ፤ ወደ እኔ እመልሳቸዋለሁ ቊጣዬ ከእነርሱ ስለ ተመለሰ፥ እኔ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤


እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።


ሂዱ፤ ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መሥዋዕትን አይደለም’ ተብሎ የተጻፈው ምን ማለት እንደ ሆነ መርምራችሁ አስተውሉ። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሓ ለመጥራት ነው” አላቸው።


እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስላችሁ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ጌታ ተመለሱ፤


跟着我们:

广告


广告