Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ጻድቅ ሰው በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ብለውም እርሱ ግን ‘የቀድሞ የጽድቅ ሥራዬ ይበቃኛል’ ብሎ ኃጢአት መሥራት ቢጀምር፥ ከቀድሞ መልካም ሥራው አንዱንም እንኳ አላስታውስለትም፤ ስለዚህም በኃጢአቱ ምክንያት ይሞታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ጻድቁን ሰው በርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ብለው፣ እርሱም ጽድቁን ተማምኖ ክፋት ቢሠራ፣ ከሠራው ጽድቅ አንዱም አይታሰብለትም፤ በኀጢአቱም ምክንያት ይሞታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እኔ ጻድቁን፦ በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ባልሁት ጊዜ፥ እርሱ ጽድቁን ተማምኖ ኃጢአት ቢሠራ በሠራው ኃጢአትም ይሞታል እንጂ ጽድቁ አይታሰብለትም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔ ጻድ​ቁን፦ በር​ግጥ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽ​ድቁ ታምኖ ኀጢ​አት ቢሠራ በሠ​ራው ኀጢ​አት ይሞ​ታል እንጂ ጽድቁ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እኔ ጻድቁን፦ በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽድቁ ታምኖ ኃጢአት ቢሠራ በሠራው ኃጢአትም ይሞታል እንጂ ጽድቁ አይታሰብለትም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:13
11 交叉引用  

“ነገር ግን ደግ ሰው መልካም ማድረጉን ትቶ ክፉ ሰዎች የሚያደርጉአቸውን ክፉና አጸያፊ ነገሮች ማድረግ ቢጀምር፥ በሕይወት መኖር የሚችል ይመስላችኋልን? አይደለም! እንዲያውም ያደረገው የደግነት ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ባለመታመኑና ኃጢአተኛም በመሆኑ ምክንያት ይሞታል።


ጻድቅ ሰው መልካም ማድረጉን ትቶ ክፉ ሥራ ሠርቶ ቢሞት የሚሞተው በኃጢአቱ ምክንያት ነው፤


የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት የእኔ ነው፤ የወላጅም ሆነ የልጅ ሕይወት የእኔ መሆኑን ዕወቁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሰው ራሱ ይሞታል።


“በደግነቱ የታወቀ ጻድቅ ሰው ክፉ ሥራ መሥራት ቢጀምርና እኔም በችግር ላይ እንዲወድቅ ባደርገው፥ አንተ ካላስጠነቀቅኸው በቀር በኃጢአቱ ይሞታል፤ ከዚያ በፊት የፈጸመው መልካም ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ስለ እርሱ ሞት አንተን በኀላፊነት እጠይቅሃለሁ።


ጻድቅ ሰው የጽድቅ ሥራውን ትቶ ክፉ መሥራትን ቢጀምር፥ ስለ ክፉ ሥራው ይሞታል፤


እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያጸድቅበትን መንገድ ባለማወቃቸው የራሳቸውን የጽድቅ መንገድ ተከተሉ እንጂ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አልተከተሉም።


ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።


የእኔ የሆነ ጻድቁ ሰው ግን በእምነት ሕይወትን ያገኛል፤ ወደ ኋላው ቢያፈገፍግ ግን እኔ በእርሱ አልደሰትም።”


እነርሱ የወጡት ከእኛ መካከል ነው። ይሁን እንጂ ዱሮውንም ከእኛ ወገን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋርም ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከእኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል።


跟着我们:

广告


广告