Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 32:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “በማታውቃቸው ሕዝቦች መካከል የጥፋትህን ዜና በማሰማበት ጊዜ የብዙ ሕዝቦችን ልብ አስጨንቃለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በማታውቀው ምድር፣ በሕዝቦች መካከል ያንተን ጥፋት ሳመጣ፣ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በማታውቃቸውም አገሮች ባሉ በአሕዛብ ዘንድ ስብራትህን ባመጣሁ ጊዜ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በማ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሀገ​ሮች በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ድል መሆ​ን​ህን በአ​ሰ​ማሁ ጊዜ የብዙ ሕዝ​ብን ልብ አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በማታውቃቸውም አገሮች ባሉ በአሕዛብ ዘንድ ጥፋትህን ባመጣሁ ጊዜ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 32:9
10 交叉引用  

አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ ፍልስጥኤማውያንም ተሸበሩ፤


“በዚህም ጊዜ የሌሎች መርከቦች ቀዛፊዎች ነጂዎችና የመርከቦቹ አዛዦች ሁሉ ወጥተው በባሕሩ ጠረፍ ቆሙ።


እነሆ ጠፋህ! ለዘለዓለምም አትገኝም፤ ያውቁህ የነበሩ አገሮች ሁሉ ተሸብረዋል፤ በአንተ ላይ የደረሰው መጥፎ ዕድል እንዳይገጥማቸውም ፈርተዋል።’ ”


ግብጽን ባድማ ከሆኑት አገሮች የበለጠ ባድማ እንድትሆን አደርጋታለሁ፤ የግብጽ ከተሞች እስከ አርባ ዓመት ፍርስራሽ ሆነው ይቀራሉ፤ ከተሞችዋም ከፈራረሱ ከተሞች አንድዋ አደርጋታለሁ፤ ግብጻውያንን ስደተኞች አደርጋቸዋለሁ፤ በሌሎች ሕዝቦች መካከልም ተበታትነው እንዲኖሩ አደርጋለሁ።”


ግብጻውያንን በሕዝቦችና በተለያዩ አገሮች መካከል እበትናቸዋለሁ።


ግብጻውያንን በሕዝቦችና በተለያዩ አገሮች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


በዚያን ቀን ‘አንዳች ነገር ይደርስብናል’ ብለው ያልተጠራጠሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራራት መልእክተኞች በእኔ ትእዛዝ ይወጣሉ፤ እነርሱም በግብጽ ላይ በእርግጥ በሚመጣው ጥፋት ምክንያት ይጨነቃሉ።”


አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”


跟着我们:

广告


广告