ሕዝቅኤል 32:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 በሕያዋን ዓለም አሸባሪዎች ስለ ነበሩ እነርሱ ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር ማለት ሰይፎቻቸው ከወደራስጌ፥ ጋሻቸው በሰውነታቸው ላይ ተደርጎ ይቀበሩ እንደ ነበሩት እንደ ቀድሞ ጦረኞች ሥርዓተ ቀብር አልተደረገላቸውም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 ከዘመናት በፊት ከወደቁት ከኀያላን ሰዎች፣ ከእነዚያ ሰይፋቸውን ተንተርሰው፣ ጋሻቸውንም ደረታቸው ላይ ይዘው ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ መቃብር ከወረዱት ጋራ አይጋደሙምን? የእነዚህ ተዋጊዎች ሽብር በሕያዋን ምድር ባሉት ያልተገረዙ ኀያላን ላይ ቢደርስም፣ የኀጢአታቸው ቅጣት በዐጥንታቸው ላይ ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ከወደቁ ኃያላን ካልተገረዙ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው፥ ሰይፋቸውንም ከራስጌያቸው በታች አድርግው ወደ ሲኦል ከወረዱ ጋር አልተኙም፥ በሕያዋንም ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ኃጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ነበር 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 በሕያዋንም ምድር ኀያላኑን ያስፈሩ ነበርና፤ መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወረዱ፥ ሰይፋቸውንም ከራሳቸው በታች ከአደረጉ፥ ኀጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወደቁ ካልተገረዙ ኀያላን ጋር ይተኛሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 በሕያዋንም ምድር ኃያላኑን ያስፈሩ ነበርና መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወረዱ፥ ሰይፋቸውንም ከራሳቸው በታች ካደረጉ፥ ኃጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወደቁ ካልተገረዙ ኃያላን ጋር ይተኛሉ። 参见章节 |