Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 32:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 “የሜሼክና የቱባል ወታደሮች ሕዝቦቻቸው መቃብሮች በዚያ ነበሩ፤ እነርሱ የተገደሉት በጦርነት ነው፤ ሁሉም በእግዚአብሔር ያላመኑ ናቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱም ከዚህ በፊት የሕያዋንን ዓለም የሚያሸብሩ ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “ሜሼኽና ቶቤል መቃብሮቻቸው በብዙ ሰራዊታቸው መቃብር ተከብበው ይገኛሉ፤ ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ፣ በሕያዋን ምድር ሽብራቸውን ስለ ነዙ በሰይፍ ተገድለዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሜሼክና ቱባል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ በሰይፍ ተገድለዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 “ሞሳ​ሕና ቶቤል፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ነው፤ ሁሉም ሳይ​ገ​ረዙ በሰ​ይፍ ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ነበ​ርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሞሳሕና ቶቤል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፥ ሁሉም ሳይገረዙ በሰይፍ ተገድለዋል፥ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ነበርና።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 32:26
11 交叉引用  

እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከል ያለውን ታላቅ ከተማ ሬሴን የተባሉትን ከተሞች መሠረተ።


የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክና፥ ቲራስ ናቸው።


ያፌትም ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክና ቲራስ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።


ከግሪኮች ከቱባልና ከሜሼክ ጋር የንግድ ሥራ ታካሂጂ ነበር፤ ባሪያዎችንና ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎችን ወስደሽ፥ በምትኩ ሸቀጥሽን ትሰጪአቸው ነበር፤


በሕያዋን ዓለም አሸባሪዎች ስለ ነበሩ እነርሱ ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር ማለት ሰይፎቻቸው ከወደራስጌ፥ ጋሻቸው በሰውነታቸው ላይ ተደርጎ ይቀበሩ እንደ ነበሩት እንደ ቀድሞ ጦረኞች ሥርዓተ ቀብር አልተደረገላቸውም።


“እርሱ በሕያዋን ዓለም ሽብርን ይነዛ ስለ ነበረ በሰይፍ በተገደሉት በእግዚአብሔር በማያምኑት መካከል ብዛት ካለው ሕዝቡ ጋር ያርፋል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሜሼክና የቱባል ሕዝብ ገዢ በሆነው በጎግ ላይ ትንቢት ተናገርበት፤ በእርሱም ላይ የተነሣሁ መሆኔን ንገረው።


跟着我们:

广告


广告