ሕዝቅኤል 32:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ለዔላም ወታደሮችና ብዛት ላለው ሕዝብዋ በሰይፍ በተገደሉት መካከል ማረፊያ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ መቃብሮቻቸውም በዙሪያው ነበሩ፤ ሁሉም በእግዚአብሔር ሳያምኑ በጦርነት የተገደሉ ናቸው፤ እነርሱም የሕያዋንን ዓለም ያሸብሩ የነበሩ በጦርነት የተገደሉ ናቸው፤ ኀፍረታቸውንም ተከናንበው ወደ ጥልቁ ከሚወርዱት ጋር አብረው ይወርዳሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 በመቃብሯ ዙሪያ ካለው መላው ሰራዊቷ ጋራ፣ በታረዱት መካከል መኝታ ተዘጋጅቶላታል። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፤ ሽብራቸው በሕያዋን ምድር ስለ ተነዛ፣ ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱት ጋራ ዕፍረታቸውን ይሸከማሉ፤ በታረዱትም መካከል ይጋደማሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 በመቃብሯ ዙሪያ በተገደሉት መካከል ከብዛትዋ ሁሉ ጋር መኝታን አድርገውላታል፤ ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፤ በሕያዋንም ምድር ያሸብሩ ነበር ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል፥ በተገደሉትም መካከል ተሰጥተዋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 በተገደሉት መካከል ከብዛቷ ሁሉ ጋር መኝታን አድርገውላታል፤ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው፤ ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፤ በሕያዋንም ምድር ያስፈሩ ነበር፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል፤ በተገደሉትም መካከል ተሰጥተዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 በተገደሉት መካከል ከብዛትዋ ሁሉ ጋር መኝታን አድርገውላታል፥ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፥ በሕያዋንም ምድር ያስፈሩ ነበር ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል፥ በተገደሉትም መካከል ተሰጥተዋል። 参见章节 |