Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 32:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 መቃብሮቻቸውም በጥልቁ መጨረሻ ነበር፤ በሕያዋን ዓለም ያሸብር የነበረውና በጦርነት ተገድለው የወደቁ የወታደሮቻቸው መቃብር በዙሪያቸው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 መቃብራቸው በጥልቁ ጕድጓድ ውስጥ ነው፤ ሰራዊቷም በመቃብሯ ዙሪያ ተረፍርፏል። በሕያዋን ምድር ሽብርን የነዙ ሁሉ ታርደዋል፤ በሰይፍም ወድቀዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 መቃብራቸው በጥልቅ ጉድጓድ በውስጠኛው ክፍል ነው፥ ጉባኤዋም በመቃብሯ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸበሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 መቃ​ብ​ራ​ቸው በጕ​ድ​ጓዱ በው​ስ​ጠ​ኛው ክፍል ነው፤ ጉባ​ኤ​ዋም በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 መቃብራቸው በጕድጓዱ በውስጠኛው ክፍል ነው፥ ጉባኤዋም በመቃብርዋ ዙሪያ ነው፥ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 32:23
14 交叉引用  

“ጥበብ ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶች በሚኖሩባት ምድር አትገኝም፤ እውነተኛ ዋጋዋንም የሚያውቅ ሰው የለም።


ስለዚህ ሕያዋን በሚገኙበት በእግዚአብሔር ፊት እኖራለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ጠባቂዬ አንተ ነህ፤ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ።


ሕያዋን በሚኖሩባት ምድር እስካለሁ ድረስ የእግዚአብሔርን በጎነት እንደማይ እተማመናለሁ።


ከተሞችን ደምስሶ ዓለምን ወደ ምድረ በዳነት የለወጣት ሰው ይህ ነውን? እስረኞች ነጻ እንዳይለቀቁና ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ የሚያደርግ እርሱ አልነበረምን?”


ሕያዋን በሚኖሩበት በዚህ ዓለም እግዚአብሔርን ወይም ከሕያው ፍጡር ሁሉ መካከል ሰውን ዳግመኛ አላይም ብዬ ነበር።


ወደ ዕርድ እንደሚሄድ የበግ ጠቦት ሆኜ ነበር፤ እነርሱ “ስሙ ዳግመኛ እንዳይታወስ ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፤ ከሕያዋያን ዓለም እናስወግደው” ብለው በእኔ ላይ ማደማቸውን አላወቅሁም ነበር።


እንዲህም እያሉ ስለ አንቺ ሙሾ ያወጣሉ፤ ‘በባሕር ጠረፍ ያሉ አገሮችን ያሸበራችሁ፥ በባሕር ላይ ኀያል የነበርሽ ዝነኛይቱ ከተማ ሆይ! እንዴት ከባሕር ጠፋሽ?


ወደ ሙታን ዓለም ወርደሽ በጥንት ዘመን ይኖሩ ከነበሩ ሕዝቦች ጋር እንድትደባለቂ አደርጋለሁ፤ ከሙታን ጋር ተወዳጅተሽ እንድትኖሪ በዚያ ከምድር በታች ባለ ዓለም ውስጥ ዘለዓለም ፈራርሰው ከቀሩ ነገሮች ጋር እተውሻለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ዳግመኛ ሰው አይኖርብሽም፤ በሕያዋንም ምድር ለመኖር ቦታ የለሽም፤


“እርሱ በሕያዋን ዓለም ሽብርን ይነዛ ስለ ነበረ በሰይፍ በተገደሉት በእግዚአብሔር በማያምኑት መካከል ብዛት ካለው ሕዝቡ ጋር ያርፋል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


እግዚአብሔር ስለ አሦራውያን የሰጠው ፍርድ እንዲህ የሚል ነው፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስማችሁን የሚያስጠራ ተተኪ ዘር አይኖራችሁም፤ በአማልክታችሁ ቤተ መቅደስ የሚገኙትን የተቀረጹ ምስሎችንና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶችን አጠፋለሁ፤ እናንተም ዋጋ ቢሶች ስለ ሆናችሁ የመቃብር ጒድጓድ እምስላችኋለሁ።”


跟着我们:

广告


广告