Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 32:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ለግብጽ ንጉሥ አልቅስለትና በብርቱም በማስጠንቀቅ እኔ የምሰጥህን እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘አንተ በአሕዛብ መካከል ስትኖር ራስህን እንደ አንበሳ አድርገህ ቈጥረሃል፤ ነገር ግን አንተ በባሕር ውስጥ እንደሚገላበጥ አስፈሪ የባሕር አውሬ ነህ፤ በእግሮችህ እያንቦጫረቅህ ውሃውን ታደፈርሳለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤ “ ‘አንተ በሕዝቦች መካከል እንደ አንበሳ፣ በባሕሮችም ውስጥ እንደ አስፈሪ አውሬ ነህ፤ በወንዞችህ የምትንቦጫረቅ፣ ውሃውን በእግርህ የምትመታ፣ ምንጮችን የምታደፈርስ ነህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈር​ዖን ሙሾ አሙሽ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ የአ​ሕ​ዛ​ብን አን​በሳ መስ​ለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነ​ሃል፤ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም ወግ​ተ​ሃል፤ ውኃ​ው​ንም በእ​ግ​ርህ አደ​ፍ​ር​ሰ​ሃል፥ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም በተ​ረ​ከ​ዝህ ረግ​ጠ​ሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በለው፦ የአሕዛብን አንበሳ መስለህ ነበር፥ ነገርግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነሃል፥ በወንዞችህም ወጥተሃል፥ ወኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 32:2
27 交叉引用  

ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤ ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥ ወደ ዋሻው ይመለሳል፤ እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤ ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው?


ሥጋው ድርብርብ ሆኖ እርስ በርሱ የተጣበቀ ስለ ሆነ ሰውነቱ እንደ ብረት የጠነከረ ነው።


“ይህን ያኽል ተጠባባቂ ያደረግህብኝ እኔ ባሕር ነኝን? ወይስ ዓሣ አንበሪ?


የክፉን ሰው ጠባይ የሚወርስ ደግ ሰው የደፈረሰን ምንጭ ወይም የተመረዘን ኲሬ ይመስላል።


ድኾችን በጭካኔ የሚገዛ መሪ እንደሚያገሣ አንበሳና ተርቦ ምግቡን ለማደን እንደሚያደባ ድብ ነው።


እነርሱም፥ በእንስሶች መካከል ብርቱ የሆኑና ከማንም ፊት የማይሸሹ አንበሶች፥


በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል።


እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።


አንበሳ ከተሸሸገበት ደን እንደሚወጣ፥ ሕዝብን ሁሉ የሚያጠፋ ይነሣል፤ እርሱም ይሁዳን ለማጥፋት ይመጣል፤ የይሁዳ ከተሞች ይፈራርሳሉ፤ የሚኖርባቸውም አይገኝም።


ይህ እንደ ዓባይ ወንዝ የሚነሣና ሞልቶ በጐርፉ ዳርቻውን ሁሉ እንደሚያጥለቀልቅ ወንዝ የሆነ ይህ ማን ነው?


እንደ ዓባይ ወንዝ የተነሣችውና ሞልቶ በጐርፉ ዳርቻውን ሁሉ እንደሚያጥለቀልቅ ወንዝ የሆነችው ግብጽ ነች፤ ግብጽ እንዲህ ብላለች ‘እኔ ተነሥቼ ዓለምን አጥለቀልቃለሁ። ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን ሕዝብ ሁሉ እደመስሳለሁ።’


ሕዝቡም እንዲህ አሉ፦ “ዐይናችን በእንባ እንዲርስ፥ በጉንጫችንም እንባው እንዲወርድ፥ አስለቃሾች በቶሎ ሙሾ እንዲያወጡ ንገሩአቸው።”


እንዲህም እያሉ ስለ አንቺ ሙሾ ያወጣሉ፤ ‘በባሕር ጠረፍ ያሉ አገሮችን ያሸበራችሁ፥ በባሕር ላይ ኀያል የነበርሽ ዝነኛይቱ ከተማ ሆይ! እንዴት ከባሕር ጠፋሽ?


“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ጢሮስ ሙሾ አውጣ፤


በሐዘናቸውም ስምሽን እያነሡ ያለቅሳሉ። ስለ አንቺም ሙሾ ያወጣሉ፤ እንዲህም ይላሉ፦ ‘በባሕር መካከል ጠፍታ እንደ ቀረች እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው?


“የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስ ንጉሥ ስለሚገጥመው መጥፎ ዕድል ሙሾ አውጣ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘በጥበብ የተሞላህና እጅግ መልከ ቀና በመሆንህ የፍጹምነት ምሳሌ ነበርክ።


እንዲያውም ከሁሉ የደከመ መንግሥት ስለሚሆን ዳግመኛ ሌሎች መንግሥታትን የመግዛት ዕድል አይኖረውም፤ ከሁሉ ያነሰ ስለማደርገው ሌላ መንግሥት ማስገበር አይችልም።


ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ በወንዝ ውስጥ የተጋደመ አስፈሪ የባሕር አውሬ የምትመስል አንተ! እነሆ፥ እኔ በቊጣ ተነሥቼብሃለሁ፤ ‘የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ትላለህ።


ይህ የሚያወርዱት ሙሾ ነው፤ የሀገሪቱ ሴቶች ሙሾ ያሰማሉ፤ ለግብጽና ብዛት ላለው ሕዝብዋ ያወርዱታል፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።”


“የሰው ልጅ ሆይ! የግብጽን ሕዝብ ከሌሎች ኀያላን ሕዝቦች ጋር ወደ ሙታን ዓለም በሙሾ ሸኛቸው።”


ከመልካሙ መሰማሪያ የተመገባችሁት አንሶ ነውን? የቀረውን መሰማሪያችሁን በእግራችሁ የምትረግጡት? የጠራ ውሃ ከጠጣችሁ በኋላ የቀረውን ማደፍረስ አለባችሁን?


ሳባና ዴዳን፥ እንዲሁም የተርሴስ ነጋዴዎችና ወጣት ጦረኞች እንዲህ ይሉሃል፦ ‘ምርኮን ለመውሰድ መጣህን? ብርንና ወርቅን፥ እንስሶችና ቈሳቊስን፥ ማለት ብዙ ምርኮን እንዲያጓጒዙልህ ብዛት ያላቸውን ሰዎችህን ሰበሰብክን?’ ”


ይህ ሕዝብ፥ ለመያዝ እንደ ተዘጋጁ ወንድ አንበሳና ሴት አንበሳ አድብቶአል፤ በተኛ ጊዜ ሊያስነሣው የሚደፍር ማነው? የሚመርቅህ የተመረቀ ይሁን፤ የሚረግምህም የተረገመ ይሁን።”


“ይህን ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የሚያውለው ሁሉ፥ ቤቱን በድንጋይ መሠረት ላይ የሠራ ብልኅ ሰውን ይመስላል።


跟着我们:

广告


广告