Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 32:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኔ ግብጽን ወና እና ባድማ በማደርግበትና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ በማጠፋበት ጊዜ፥ አንተና ሕዝብህ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ግብጽን ባድማ ሳደርጋት፣ ምድሪቱም ያላትን ሁሉ ያጣች ስትሆን፣ በዚያም የሚኖሩትን ሁሉ ስመታ፣ ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የግብጽንም ምድር ወና እና ባድማ ባደረግሁ ጊዜ፥ ሞላዋንም ያጣች ምድር ባደረግኋት ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በመታሁ ጊዜ፥ እኔ ጌታ እንደሆንኩ ያውቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የግ​ብ​ፅ​ንም ምድር ባድ​ማና ውድማ በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ ምድ​ርም በመ​ላዋ በጠ​ፋች ጊዜ፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ት​ንም ሁሉ በቀ​ሠ​ፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የግብጽንም ምድር ባድማና ውድማ ባደረግሁ ጊዜ፥ ሞላዋንም ያጣች ምድር ባደረግኋት ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በቀሠፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 32:15
13 交叉引用  

ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ የእርሱ ናቸው።


እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።


እነርሱንም በማሸንፍበት ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።


በዚህ ዐይነት የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አንሥቼ እስራኤላውያንን ከአገራቸው በማወጣበት ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


ግብጽን ባድማ ከሆኑት አገሮች የበለጠ ባድማ እንድትሆን አደርጋታለሁ፤ የግብጽ ከተሞች እስከ አርባ ዓመት ፍርስራሽ ሆነው ይቀራሉ፤ ከተሞችዋም ከፈራረሱ ከተሞች አንድዋ አደርጋታለሁ፤ ግብጻውያንን ስደተኞች አደርጋቸዋለሁ፤ በሌሎች ሕዝቦች መካከልም ተበታትነው እንዲኖሩ አደርጋለሁ።”


ግብጽን በዚህ ዐይነት በምቀጣበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


ግብጻውያንን በሕዝቦችና በተለያዩ አገሮች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


ውሃዎችህ እንዲጠሩ፥ ወንዞችህም እንደ ዘይት በሰላም እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


የተገደሉት በአካባቢያችሁ ይጣላሉ፤ ከዚያ በኋላ እናንተ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


跟着我们:

广告


广告