ሕዝቅኤል 31:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 አንተ የተዋቡ ጥላማ ቅርንጫፎች እንዳሉትና የቁመቱም ርዝመት ደመናዎችን እንደሚነካ የሊባኖስ ዛፍ ነህ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ለጫካው ጥላ የሆኑ የሚያማምሩ ቅርንጫፎች የነበሩትን፣ እጅግ መለሎ ሆኖ፣ ጫፉ ሰማይ የደረሰውን፣ የሊባኖስን ዝግባ አሦርን ተመልከት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እነሆ አሦር ቅርጫፉ የተዋበ፥ ጥላ የሚሰጥ ጫካ፥ ቁመቱ የረዘመ፥ ጫፉም በቅርንጫፎች መካከል የነበረ የሊባኖስ ዝግባ ነበረ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍግነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመናዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እነሆ፥ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍግነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም በደመናዎች መካከል እንደ ነበረ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ነበረ። 参见章节 |