Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 31:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “ዛፉ የግብጽ ንጉሥና የሕዝቡ ሁሉ ምሳሌ ነው፤ በዔደን ገነት ከነበሩት ዛፎች መካከል እንኳ በቁመትና በውበት እርሱን የሚያኽል አልነበረም። አሁን ግን በዔደን ገነት እንደ ነበሩት ዛፎች ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳል፤ እዚያም በእግዚአብሔር የማያምኑ በጦርነት ከተገደሉት ሁሉ ጋር ይደባለቃል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ ‘በዔድን ካሉት ዛፎች በውበትና በትልቅነት የሚወዳደርህ የትኛው ነው? ይሁን እንጂ አንተም እንደዚሁ ከዔድን ዛፎች ጋራ ከመሬት በታች ትወርዳለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት፣ ካልተገረዙትም መካከል ትጋደማለህ። “ ‘እንግዲህ ፈርዖንና ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝቡ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በክብርና በታላቅነት ከዔድን ዛፎች መካከል እንግዲህ ማንን ትመስላለህ? ሆኖም ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ትወርዳለህ፥ በሰይፍ በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትጋደማለህ። ይህም ፈርዖንና ብዛቱ ሁሉ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “በክ​ብ​ርና በታ​ላ​ቅ​ነት በዔ​ድን ዛፎች መካ​ከል ማንን ትመ​ስ​ላ​ለህ? ነገር ግን ከዔ​ድን ዛፎች ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም በተ​ገ​ደ​ሉት ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ትተ​ኛ​ለህ። ይህም ፈር​ዖ​ንና የሕ​ዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በክብርና በታላቅነት በዔድን ዛፎች መካከል ማንን መስለሃል? ነገር ግን ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ያወርዱሃል፥ በሰይፍም በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትተኛለህ። ይህም ፈርዖንና የሕዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 31:18
19 交叉引用  

የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፥ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ ይህን ወሬ በጋት አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ አታውጁ።


አካዝ፥ ችግሩ እየባሰበት በሄደ ጊዜ ከምንጊዜውም ይበልጥ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ።


ሌሎችን በማጥፋት ብርቱ የሆነ፥ በታላቅ ሀብቱ የተመካና፥ ብርታቱን በእግዚአብሔር ላይ ያላደረገ ሰው ይኸውላችሁ።


በውጪ አገር ሰዎች እጅ በእግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎችን ሞት ትሞታለህ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”


የቱንም ያኽል ውሃ እየጠጣ ቢያድግ በዚህ ዐይነት ከፍተኛ ቁመት እስከ ደመና የሚደርስ ዛፍ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አይኖርም። ሟቾች በሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሰው የሞት ፍርድ በእነርሱም ላይ ይደርሳል፤ ወደ ሙታን ዓለምም ይወርዳሉ።”


እኔ ያን ዛፍ ወደ ሙታን ዓለም እንዲወርድ በማደርግበት ጊዜ አወዳደቁ የሚያሰማው ድምፅ ሕዝቦችን ሁሉ ያንቀጠቅጣል፤ ወደ ሙታን ዓለም የወረዱ የዔደን ዛፎችና የጥሩ መስኖ ውሃ የሚጠጡ የተመረጡ የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እርሱ ወደ ሙታን ዓለም በመውረዱ ደስ ይላቸዋል፤


“የሰው ልጅ ሆይ! ለግብጽ ንጉሥና ብዛት ላለው ሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገር፥ ‘በታላቅነት ከማን ጋር ትመሳሰላለህ?


በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ያለው የሊባኖስ ዛፍ ሊወዳደረው አይችልም፤ የጥድ ዛፍም ቅርንጫፉን አያኽልም፤ የግራር ዛፎች ቅርንጫፍ ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር ሲወዳደር እንደ ኢምንት ነው። በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካሉ ዛፎች መካከል አንዳቸው እንኳ እንደ እርሱ ያለ ውበት የላቸውም።


እኔ እርሱን በተንሠራፉ ቅርንጫፎች የተዋበ አደረግሁት፤ እርሱ እኔ እግዚአብሔር በተከልኳት በዔደን ገነት ያለውን ዛፍ ሁሉ የሚያስቀና ነበር።’


ብዙ ሕዝቦች አንተን አይተው እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ ሰይፌን በፊታቸው በማነሣበት ጊዜ ንጉሦቻቸው በአንተ ምክንያት በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤ አንተ በምትወድቅበት ቀን እያንዳንዳቸው በየጊዜው ለሕይወታቸው በመፍራት ይርበደበዳሉ።”


እንዲህም በላቸው፦ “ውበታችሁ ከማን ይበልጥ ይመስላችኋል? ወደ ታች ወርዳችሁ በእግዚአብሔር ከማያምኑ ጋር ተጋደሙ።


ግብጻውያን ወደ ሙታን ዓለም በሚወርዱበት ጊዜ በሙታን ዓለም ውስጥ የነበሩ ታላላቅ አርበኞች አቀባበል ያደርጉላቸዋል፤ ሲቀበሉአቸውም ‘እናንተ ከተባባሪዎች ጋር ኑ ውረዱ! በጦርነት ከተገደሉት በእግዚአብሔር ከማያምኑ ጋር ተጋደሙ!’ ይሉአቸዋል።


በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ቃል ሰምቶ የማያስተውለውን ሰው ነው፤ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልቡ የተዘራውን ቃል ይወስድበታል፤


እንግዲህ ወዳጆቼ ሆይ! ጣዖትን ከማምለክ ራቁ።


ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እስራኤልን ከዚህ አሳፋሪ ውርደት ለሚያድን ሰው ምን ይደረግለታል? ኧረ ለመሆኑ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት የሚፈታተን ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።


እኔ ያንተ አሽከር አንበሳና ድብ ገድያለሁ፤ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ስለ ተፈታተነ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告