Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 31:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔ ያን ዛፍ ወደ ሙታን ዓለም እንዲወርድ በማደርግበት ጊዜ አወዳደቁ የሚያሰማው ድምፅ ሕዝቦችን ሁሉ ያንቀጠቅጣል፤ ወደ ሙታን ዓለም የወረዱ የዔደን ዛፎችና የጥሩ መስኖ ውሃ የሚጠጡ የተመረጡ የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እርሱ ወደ ሙታን ዓለም በመውረዱ ደስ ይላቸዋል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ወደ ጕድጓድ ከሚሄዱት ጋራ ወደ መቃብር ባወረድሁት ጊዜ ሲወድቅ በተሰማው ድምፅ አሕዛብ ደነገጡ። ከዚያም የዔድን ዛፎች ሁሉ፣ ምርጥና ልዩ የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች፣ ውሃ የጠገቡትም ዛፎች ሁሉ ከምድር በታች ሆነው ተጽናኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣልሁት ጊዜ ከመውደቁ ድምፅ የተነሣ ሕዝቦችን አንቀጠቀጥሁ፤ ውኃ የሚጠጡ ሁሉ፥ ምርጦችና መልካሞች የሊባኖስ ዛፎች፥ የዔድን ዛፎች ሁሉ በታችኛው ምድር ውስጥ ተጽናንተዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣ​ል​ሁት ጊዜ ከመ​ው​ደቁ ድምፅ የተ​ነሣ አሕ​ዛ​ብን አን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥሁ፤ ውኃም የሚ​ጠጡ ሁሉ፥ ምር​ጦ​ችና መል​ካ​ሞች የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፥ የዔ​ድን ዛፎች ሁሉ በታ​ች​ኛው ምድር ውስጥ ተጽ​ና​ን​ተ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣልሁት ጊዜ ከመውደቁ ድምፅ የተነሣ አሕዛብን እንቀጠቀጥሁ፥ ውኃም የሚጠጡ ሁሉ፥ ምርጦችና መልካካሞች የሊባኖስ ዛፎች፥ የዔድን ዛፎች ሁሉ በታችኛው ምድር ውስጥ ተጽናንተዋል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 31:16
20 交叉引用  

ነገር ግን ወደ ሙታን ዓለም፥ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ወርደሃል።


የሊባኖስ ዛፎችና ዝግባዎች እንኳ ስለ ወደቀው ንጉሥ ደስታቸውን ይገልጣሉ፤ እርሱ ስለ ተወገደ ከእንግዲህ ወዲህ በእነርሱ ላይ መጥረቢያ የሚያነሣባቸው ሰው አይኖርም።


የባቢሎን መያዝ ዜና ሲሰማ ምድር ትናወጣለች፤ ጩኸትዋም በሕዝቦች መካከል ይሰማል።”


ሆኖም በኢየሩሳሌም ውስጥ ከእርስዋ ወደ እናንተ የሚመጡ ቅሬታዎች ይቀሩላታል፤ አካሄዳቸውንና ተግባራቸውን በምታዩበት ጊዜ የእነርሱን ሁኔታ ትረዳላችሁ፤ እናንተም በእነርሱ ላይ ያደረስኩት መቅሠፍት ሁሉ ያለምክንያት እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


በፈረሶቻቸው ኮቴ የሚነሣው አቧራ እንደ ደመና ሆኖ ይሸፍንሻል፤ እርሱ ወደ ቅጥር በሮችሽ በሚገባበት ጊዜ ከፈረሰኛው፥ ከሠረገላውና ከመንኰራኲሩ የሚሰማው ድምፅ ተጥሳ እንደሚገባባት ከተማ ቅጥሮችሽን ያናጋል።


ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ከተማ እንዲህ ይላታል፦ “ቊስለኞች ሲቃትቱና በመካከልሽ ግድያ ሲካሄድ ባወዳደቅሽ ድምፅ የጠረፉ አካባቢ አይናወጥምን?


መርከበኞቹ ወደ ባሕር ሲሰጥሙ ያሰሙት ጩኸት በባሕር ዳር ያሉትን አገሮች አንቀጠቀጡ።


የቱንም ያኽል ውሃ እየጠጣ ቢያድግ በዚህ ዐይነት ከፍተኛ ቁመት እስከ ደመና የሚደርስ ዛፍ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አይኖርም። ሟቾች በሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሰው የሞት ፍርድ በእነርሱም ላይ ይደርሳል፤ ወደ ሙታን ዓለምም ይወርዳሉ።”


“ዛፉ የግብጽ ንጉሥና የሕዝቡ ሁሉ ምሳሌ ነው፤ በዔደን ገነት ከነበሩት ዛፎች መካከል እንኳ በቁመትና በውበት እርሱን የሚያኽል አልነበረም። አሁን ግን በዔደን ገነት እንደ ነበሩት ዛፎች ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳል፤ እዚያም በእግዚአብሔር የማያምኑ በጦርነት ከተገደሉት ሁሉ ጋር ይደባለቃል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


አንተ የተዋቡ ጥላማ ቅርንጫፎች እንዳሉትና የቁመቱም ርዝመት ደመናዎችን እንደሚነካ የሊባኖስ ዛፍ ነህ።


በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ያለው የሊባኖስ ዛፍ ሊወዳደረው አይችልም፤ የጥድ ዛፍም ቅርንጫፉን አያኽልም፤ የግራር ዛፎች ቅርንጫፍ ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር ሲወዳደር እንደ ኢምንት ነው። በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካሉ ዛፎች መካከል አንዳቸው እንኳ እንደ እርሱ ያለ ውበት የላቸውም።


እኔ እርሱን በተንሠራፉ ቅርንጫፎች የተዋበ አደረግሁት፤ እርሱ እኔ እግዚአብሔር በተከልኳት በዔደን ገነት ያለውን ዛፍ ሁሉ የሚያስቀና ነበር።’


ወታደሮች ቀያይ ጋሻዎችን አንግበዋል፤ ወታደሮቹ ሐምራዊ ልብስ ለብሰዋል፤ እርሱ ሲያሰልፋቸው የሠረገላዎቹ ብረት ያንጸባርቃል፤ ፈረሰኞቹ በፈረስ ላይ ሆነው ይቊነጠነጣሉ።


በሊባኖስ ላይ ያደረስከው ዐመፅ ይደርስብሃል፤ በእንስሶች ላይ ያደረግኸው ጥፋት ያስደነግጥሃል፤ ይህም የሚሆነው ሰውን ስለ ገደልክ፥ አገሮችንና ከተሞችን፥ በእነርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ ስላጠፋህ ነው።


መንግሥታትን ሁሉ እገለብጣለሁ፤ ሀብታቸውንም ሁሉ ወደዚህ እንዲመጣ አደርጋለሁ፤ ስለዚህም ቤተ መቅደሱ በሀብት የተሞላ ይሆናል።


በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ፈራረሰ፤ በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ የሰማይንም አምላክ አከበሩ።


跟着我们:

广告


广告