ሕዝቅኤል 30:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሚግዶል ጀምሮ እስከ አስዋን ድረስ የግብጽ ደጋፊዎች በጦርነት ያልቃሉ፤ የግብጽም ዕብሪተኛ ኀይል ይዋረዳል። እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 “ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የግብጽ ተባባሪዎች ይወድቃሉ። የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል። ከሚግዶል እስከ አስዋን፣ በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ጌታ እንዲህ ይላል፦ ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ የኃይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴቬኔ ድረስ በእርሷ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 “እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ግብፅን የሚደግፉ ይወድቃሉ፤ የኀይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔ ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ የኃይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፥ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节 |