Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ያም ጦርነት ከኢትዮጵያ፥ ከሊብያ፥ ከልድያ፥ ከሊቢያ፥ ከዐረብ አገር፥ በቃል ኪዳን የእኔ ወገኖች ከሆኑት ሕዝብ መካከል እንኳ ተቀጥረው የመጡትን ሁሉ የሚፈጅ ይሆናል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ሉድም መላው ዐረብ፣ ሊብያና የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብጽ ጋራ በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ኢትዮጵያ፥ ፉጥ፥ ሉድ፥ ባዕዳን ሁሉ፥ ኩብና የቃል ኪዳኑ ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ኢት​ዮ​ጵ​ያና ፉጥ፥ ሉድም፥ ዓረ​ብም ሁሉ፥ ኩብም፤ ሊብ​ያም፤ ቀር​ጤ​ስም የተ​ደ​ባ​ለቀ ሕዝ​ብም ሁሉ፥ ቃል ኪዳ​ን​ንም የገ​ባ​ችው ምድር ልጆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ኢትዮጵያና ፉጥ ሉድም የተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:5
13 交叉引用  

እርሱም አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሠረገሎችና ሥልሳ ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሺሻቅ ጦር ሠራዊት ውስጥ ከእርሱ ጋር ከግብጽ የመጡ ብዛታቸው ሊቈጠር የማይቻል ሊቢያውያን፥ ሱካውያንና ኢትዮጵያውያን ነበሩ፤


ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የክንፎች ድምፅ ለሚሰማባት አገር ወዮላት!


የአሦር ንጉሠ ነገሥት ለግብጻውያን ኀፍረት ይሆን ዘንድ መቀመጫዎቻቸው ሳይሸፈኑ ወጣቶችም ሆኑ ሽማግሌዎች ዕራቊታቸውንና ባዶ እግራቸውን ሆነው ግብጾችንና ኢትዮጵያውያንን በምርኮ ይመራቸዋል።


ደግ ነገር ሳይሆን ክፉ ነገር እንዲደርስባችሁ አደርጋለሁ፤ ከእናንተ አንድ እንኳ ሳይተርፍ ሁላችሁም በጦርነትና በረሀብ ትሞታላችሁ፤


ፈረሶች ወደ ፊት እንዲሄዱ፥ ሠረገሎችም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እንዲሽከረከሩ እዘዙ፤ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ ጋሻቸውን አንግበው በመጡ ሰዎችና፥ ከልድያ በመጡ ቀስት በሚወረውሩ ኀያላን ሰዎች ጭምር የተጠናከሩ ወታደሮችን ላኩ” ይላል እግዚአብሔር።


በፈረሶቻቸው፥ በሠረገሎቻቸውና በቅጥር ወታደሮቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዝ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሁኑ፤ በሀብታሞቹ ላይ ሰይፍ መዛችሁ ሀብታቸውን ሁሉ ዝረፉ!


“ከፋርስ፥ ከልድያና ከሊቢያ የመጡ ወታደሮች በሠራዊትሽ ውስጥ ያገለግላሉ፤ ጋሻቸውንና የራስ ቊራቸውን በጦር ሰፈርሽ ሰቅለዋል፤ እነርሱ ለአንቺ ክብር ያስገኙ ሰዎች ናቸው።


ከፋርስ፥ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ የመጡ ሰዎችም ሁሉ ጋሻ አንግበው የራስ ቊር ደፍተው የእርሱ ተባባሪዎች በመሆን ከእርሱ ጋር ተሰልፈዋል።


የግብጽን ወርቅ፤ ብርና ሌላውንም የከበረ ነገር ሁሉ ከተደበቀበት ቦታ ይወስዳል፤ ሊቢያንና ኢትዮጵያንም ድል ያደርጋል፤


እናንተም ኢትዮጵያውያን በሰይፌ ትገደላላችሁ።


跟着我们:

广告


广告