Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በዚህም ዐይነት የባቢሎንን ንጉሥ ኀይል በማጠንከር የእኔን ሰይፍ በእጁ አስይዘዋለሁ። የግብጽን ንጉሥ ኀይል ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም ለሞት የሚያደርስ ቊስል እንደ ደረሰበት ሰው በጠላቱ ፊት ይቃትታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ አኖራለሁ፤ የፈርዖንንም ክንድ እሰብራለሁ፥ እሱም በፊቱ ክፉኛ እንደቆሰለ ሰው ያቃስታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አበ​ረ​ታ​ለሁ፤ ሰይ​ፌ​ንም በእጁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ግብ​ፅ​ንም ይወ​ጋ​በ​ታል፥ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ሰለ​ባ​ዋ​ንም ይሰ​ል​ባል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ፥ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፥ ተወግቶም በሚሞተው እንጕርጕሮ በፊቱ ያንጐራጕራል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:24
21 交叉引用  

በዚህም ዐይነት ሥራውን እንድናቆም ለማድረግ ያስፈራሩን ነበር፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እባክህ አበርታኝ!” ስል ጸለይኩ።


በየከተማው ለመሞት የሚያጣጥሩ ሰዎች ይቃትታሉ፤ የቈሰሉትም ሰዎች ርዳታ በመጠየቅ ይጮኻሉ። እግዚአብሔር ግን በእነርሱ ላይ የተሠራውን ግፍ አልተመለከተም።


መጠጊያዬ እግዚአብሔር ይመስገን! ለሰልፍ ያሠለጥነኛል፤ ለጦርነትም ያዘጋጀኛል።


እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ሕይወቴን ከክፉዎች አድን።


ብርታትን የሚሰጠኝና መንገዴን የሚያቀናልኝ እግዚአብሔር ነው።


ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ።


መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም።


ሕዝቦች በሥልጣኑ ሥር እንዲገዙ ለማድረግ፥ ነገሥታትን ከሥልጣን እንዲያወርድ፥ የከተሞችን ቅጽር በሮች ይከፍትለት ዘንድ ቀኝ እጁን ለያዘውና ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥ ቂሮስን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፦


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አንተ እኔን ባታውቀኝም እንኳ ብርታትን እሰጥሃለሁ።


እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው። በባቢሎን ጣዖቶች ላይ የምፈርድበትና በሀገሪቱም የሚገኙ ቊስለኞች የጭንቀት ድምፅ የሚያሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤


ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ከተማ እንዲህ ይላታል፦ “ቊስለኞች ሲቃትቱና በመካከልሽ ግድያ ሲካሄድ ባወዳደቅሽ ድምፅ የጠረፉ አካባቢ አይናወጥምን?


ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ ‘የግብጽን ምድር ለንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም ለሠራዊቱ እንደ ደመወዝ ይሆንለት ዘንድ በዘረፋና በብዝበዛ የሚያገኘውን ሀብት ሁሉ ይዞ ይሄዳል።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽን ብዙ ሕዝብ ያወድም ዘንድ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እልከዋለሁ።


እርሱም ምሕረት የሌለውን ጨካኝ ሠራዊቱን አስከትሎ ምድሪቱን ለመደምሰስ ይመጣል። እነርሱም ግብጽን በሰይፍ ይመታሉ። አገሪቱም በሬሳ የተሞላች ትሆናለች።


“የሰው ልጅ ሆይ! እኔ የግብጽን ንጉሥ ክንድ ሰብሬአለሁ፤ በሸምበቆ ጠግኖ በጨርቅ በመጠቅለል መልሶ የሚያድነው ወጌሻ የለም፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ብርታት አግኝቶ ሰይፍ ማንሣት አይችልም።


የግብጽን ንጉሥ በማዳከም የባቢሎንን ንጉሥ አበረታለሁ። እኔ ለባቢሎን ንጉሥ የምሰጠውንም ሰይፍ ወደ ግብጽ በሚቃጣበት ጊዜ ሰው ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃል።


እናንተም ኢትዮጵያውያን በሰይፌ ትገደላላችሁ።


跟着我们:

广告


广告