Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህም የተነሣ እኔ ጌታ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ እነሆ፥ እኔ የግብጽን ንጉሥ በቊጣ ተነሥቼበታለሁ፤ ስለዚህም ሁለት እጆቹን፥ ማለትም ከዚህ በፊት የተሰበረውንና ደኅነኛውን ጭምር ልሰብር ተዘጋጅቻለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነሥቻለሁ፤ ደኅናውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ነኝ፥ የበረታችውንና የተሰበረችውን ክንዱን እሰብራለሁ፥ ሰይፉንም ከእጁ እጥለዋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ላይ ነኝ የጸ​ና​ች​ው​ንና የተ​ሰ​በ​ረ​ች​ው​ንም ክን​ዱን እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ሰይ​ፉ​ንም ከእጁ አስ​ጥ​ለ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ነኝ፥ የጸናችውንና የተሰበረችውንም ክንዱን እሰብራለሁ፥ ሰይፉንም ከእጁ አስረግፈዋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:22
8 交叉引用  

የባቢሎን ንጉሥ ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ግብጽ ሰሜናዊ ጠረፍ ድረስ የግብጽ ይዞታ የነበረውን ሁሉ በቊጥጥሩ ሥር አድርጎ ስለ ነበረ የግብጽ ንጉሥና ሠራዊቱ ከዚያን በኋላ ከግብጽ ውጪ ዘመቻ አላደረጉም፤


የክፉዎች ኀይል ይሰበራል ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ያበረታቸዋል።


ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ በወንዝ ውስጥ የተጋደመ አስፈሪ የባሕር አውሬ የምትመስል አንተ! እነሆ፥ እኔ በቊጣ ተነሥቼብሃለሁ፤ ‘የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ትላለህ።


“የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትን እመልሳለሁ፤ የተሰበሩትን እጠግናለሁ፤ ደካሞችን አበረታለሁ፤ እኔ ትክክለኛ እረኛ ስለ ሆንኩ በግፍ የሰቡትንና ብርቱዎች የሆኑትን አጠፋለሁ።


መንጋውን ለከዳ ለእንዲህ ዐይነቱ ዋጋቢስ እረኛ ወዮለት! ክንዱና ቀኝ ዐይኑ በሰይፍ ይመታ፤ ክንዱ በፍጹም ይድረቅ፤ ቀኝ ዐይኑም ጨርሶ ይጥፋ።”


跟着我们:

广告


广告