Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በግብጽ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ ፔሉስየምም በብርቱ ትጨነቃለች፤ የቴብስ የቅጽር ግንቦች ይፈራርሳሉ፤ በሜምፊስም ከተማ ላይ የማያቋርጥ ሥቃይ ይደርስባታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በግብጽ ላይ እሳት አነድዳለሁ፤ ሲን በጭንቅ ትናጣለች፤ ቴብስ በማዕበል ትወሰዳለች፤ ሜምፊስ በማያቋርጥ ጭንቀት ውስጥ ትገባለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በግብጽ እሳትን አነድዳለሁ፥ ሲን ትጨነቃለች፥ ኖ ትሰባበራለች፥ ኖፍ በቀን ጠላቶች ያጠቁአታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በግ​ብ​ፅም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ሲንም ትታ​ወ​ካ​ለች፤ ኖእም ትሰ​በ​ራ​ለች፤ ሜም​ፎ​ስም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በግብጽም እሳትን አነድዳለሁ፥ ሲንም ትጨነቃለች ኖእም ትሰበራለች፥ በሜምፎስም በየቀኑ ጠላቶች ይሆኑባታል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:16
9 交叉引用  

በሰሜን ግብጽ ውስጥ ሚግዶል፥ ጣፍናስና ሜምፊስ ተብለው በሚጠሩት ከተሞችና በአገሪቱም ደቡባዊ ክፍል ተበታትነው ስለሚኖሩት እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤


በመግዛትና በመሸጥ ከፈጸምከው በደል የተነሣ የአምልኮ ስፍራዎችህ ሁሉ ረከሱ፤ ስለዚህ በከተማይቱ የሰደድ እሳት እንዲነሣ አድርጌ በሙሉ አቃጠልኳት፤ አሁን ወደ አንተ የሚመለከቱ ሁሉ ዐመድ ብቻ መሆንክን ያያሉ፤


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሜምፊስ ያሉትን ጣዖቶችና የሐሰት አማልክት ሁሉ አወድማለሁ፤ በግብጽ ምድር ላይ ገዢ ሆኖ የሚነሣ አይኖርም፤ በሕዝቡም ላይ ፍርሀትን አወርዳለሁ።


በደቡባዊ ግብጽ ጳጥሮስ የተባለውን ከተማ ባድማ አደርጋለሁ፤ በሰሜን በኩል በምትገኘው በጾዓን ከተማ ላይም እሳት አቀጣጥላለሁ፤ የቴብስንም ከተማ በፍርድ እቀጣለሁ።


የግብጽ ዋና ምሽግ የሆነችው የፔሉስየም ከተማ የቊጣዬ መዓት እንዲወርድባት አደርጋለሁ፤ የቴብስን ብዙ ሕዝብ ሁሉ እገድላለሁ።


በኦንና በቡባስቲስ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች ሁሉ በጦርነት ያልቃሉ። የከተሞቹዋ ኗሪዎችም ተማርከው ይወሰዳሉ።


በማጎግ ምድርና በባሕር ዳርቻዎች ሰዎች ያለ ስጋት በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ እሳት አቀጣጥላለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።


እነሆ ከጥፋት ለማምለጥ ሲሸሹ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ትቀብራቸዋለች፤ ያከማቹት የብር ሀብት ሁሉ ሳማ ለብሶ ይቀራል፤ መኖሪያቸውም እሾኽ ይበቅልበታል።


跟着我们:

广告


广告