Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሜምፊስ ያሉትን ጣዖቶችና የሐሰት አማልክት ሁሉ አወድማለሁ፤ በግብጽ ምድር ላይ ገዢ ሆኖ የሚነሣ አይኖርም፤ በሕዝቡም ላይ ፍርሀትን አወርዳለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ጣዖታትን አጠፋለሁ፤ በሜምፊስ ያሉትን ምስሎች እደመስሳለሁ። ከእንግዲህ በግብጽ ገዥ አይኖርም፣ በምድሪቱም ላይ ፍርሀት እሰዳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶችን አስወግዳለሁ፥ ምስሎችንም ከኖፍ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከግብጽ ምድር ገዢ አይነሳም፥ በግብጽ ምድር ላይ ፍርሃትን አኖራለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣዖ​ቶ​ቹን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም ከሜ​ም​ፎስ እሽ​ራ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ያም በግ​ብፅ ምድር አለቃ አይ​ሆ​ንም፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ፍር​ሀ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶቹን አጠፋለሁ ምስሎችንም ከሜምፎስ እሽራለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲያ በግብጽ ምድር አለቃ አይሆንም፥ በግብጽም ምድር ላይ ፍርሃትን አደርጋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:13
18 交叉引用  

“በዚያችም ሌሊት እኔ በግብጽ ምድር ሁሉ እየተላለፍኩ እያንዳንዱን የሰውም ሆነ የእንስሳ ዘር የሆነውን የበኲር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽንም አማልክት ሁሉ እቀጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


“ጣዖቶች ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ መሆናቸውንና አንተ እግዚአብሔር ጣዖቶችን ሁሉ እንደምትደመስስ ንገራቸው” አልከኝ።


የሜምፊስና የጣፊናስ ሰዎች፥ መኻል አናትሽን ይላጩሻል።


በግብጽ የጣዖትን ቤተ መቅደሶች ያቃጥላል፤ ጣዖቶቹን ይማርካል፤ እረኛ ለምዱን እንደሚደርብ ግብጽን በግዛቱ ላይ ደርቦ ምንም ጒዳት ሳይደርስበት በድል አድራጊነት ይወጣል።


በግብጽ ውስጥ በሄሊዮፖሊስ ከተማ የሚገኙትን ከድንጋይ የተሠሩ ሐውልቶችን ይደመስሳል፤ የግብጻውያንን ጣዖቶችንና ቤተ መቅደሶችን ያቃጥላል።”


በሰሜን ግብጽ ውስጥ ሚግዶል፥ ጣፍናስና ሜምፊስ ተብለው በሚጠሩት ከተሞችና በአገሪቱም ደቡባዊ ክፍል ተበታትነው ስለሚኖሩት እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤


“የግብጽ ከተሞች በሆኑት በሚግዶል፥ በሜምፊስ በጣፍናስ ይህን ቃል ዐውጅ፤ ‘ራሳችሁን ለመከላከል ተዘጋጁ፤ በዙሪያችሁ ያለው ሁሉ በጦርነት ይጠፋል።


የግብጽ ሕዝብ ሆይ! ተማርካችሁ የምትሄዱ ስለ ሆነ ዕቃችሁን አዘጋጁ፤ ሜምፊስ ፈራርሳ ሰው የማይኖርባት በረሓ ትሆናለች፤


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ግብጽን፥ አማልክትዋንና ነገሥታቶችዋን፥ የቴብስ አምላክ የሆነውን አሞንን፥ የግብጽን ንጉሥና በእርሱ የሚተማመኑትን ሁሉ እቀጣለሁ።


“ነገር ግን ይህ የማየው ነገር ምንድን ነው? ከፍርሃት የተነሣ ወደ ኋላ በመመለስ ላይ ናቸው፤ ወታደሮቻቸው ድል ሆኑ፤ በየአቅጣጫው ፍርሀትና ሽብር ስላለ ወደ ኋላ መለስ ብለው ሳያዩም ወደ ፊት ሸሹ።


በግብጽ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ ፔሉስየምም በብርቱ ትጨነቃለች፤ የቴብስ የቅጽር ግንቦች ይፈራርሳሉ፤ በሜምፊስም ከተማ ላይ የማያቋርጥ ሥቃይ ይደርስባታል።


እነሆ ከጥፋት ለማምለጥ ሲሸሹ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ትቀብራቸዋለች፤ ያከማቹት የብር ሀብት ሁሉ ሳማ ለብሶ ይቀራል፤ መኖሪያቸውም እሾኽ ይበቅልበታል።


በምድራቸው ያሉትን ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በማጥፋቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በባሕር ጠረፍና በደሴቶች የሚኖሩ መንግሥታት ሁሉ በያሉበት ለእርሱ ይሰግዳሉ።


በመከራ ባሕር ውስጥ ሲያልፉ እኔ እግዚአብሔር ማዕበሉን እመታለሁ፤ ጥልቅ የሆነውም የዓባይ ወንዝ ይደርቃል፤ ትዕቢተኛይቱ አሦር ትዋረዳለች፤ ግብጽም በትረ መንግሥትዋን ታጣለች።


በዚያን ጊዜ የጣዖቶችን ስሞች ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ፤ ዳግመኛም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ የጣዖት ነቢያትንና ርኩሳን መናፍስትን አስወግዳለሁ።


跟着我们:

广告


广告