Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እኔ ግን አንተን እንደ እነርሱ እልኸኛና የማትበገር አደርግሃለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነሆ እኔ በእነርሱ ፊት የማትበገር ጠንካራ አደርግሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነሆ፥ ፊትህን በፊታቸው ግምባርህንም በግምባራቸው አጠንክሬአለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነሆ ፊት​ህን በፊ​ታ​ቸው አጸ​ና​ሁት፤ ኀይ​ል​ህ​ንም ከኀ​ይ​ላ​ቸው ይልቅ አጸ​ና​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነሆ፥ ፊትህን በፊታቸው ግምባርህንም በግምባራቸው አጠንክሬአለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 3:8
13 交叉引用  

አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አዎ! አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ራስህን ለኃጢአት ሸጠሃል፤


ጌታ እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልተዋረድኩም፤ ራሴን እንደ ጠንካራ ድንጋይ አበረታሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።


ኤርምያስ ሆይ! እነሆ አድምጠኝ! በዚህ ምድር የሚኖሩ ሁሉ፥ ይህም ማለት የይሁዳ ነገሥታት ባለሥልጣኖች፥ ካህናቱና ሕዝቡም ሳይቀሩ በአንተ ላይ በጠላትነት ይነሡብሃል፤ ይሁን እንጂ እነርሱን ለመቋቋም የሚያስችልህን ኀይልና ብርታት እሰጥሃለሁ፤ እንደ ተመሸገች ከተማ፥ እንደ ብረት ምሰሶና ከነሐስ እንደ ተሠራ ግንብ ጠንካራ አደርግሃለሁ፤ እኔ ከአንተ ጋር ሆኜ በመጠበቅ ስለምከላከልልህ እነርሱ ከቶ ሊያሸንፉህ አይችሉም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


እነርሱን መቋቋም እንድትችል እንደ ነሐስ ግንብ አበረታሃለሁ፤ አንተን ለማዳንና ለመታደግ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አደጋ ቢጥሉብህም እንኳ አያሸንፉህም።


እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።


ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ልበ ደንዳኖችና እልኸኞች ስለ ሆኑ እኔን ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ አንተንም አይሰሙህም።


አንዳችም የሚገታህ ነገር እስከማይኖር ድረስ መልእክቴን ለመናገር ቈራጥ ትሆናለህ፤ አንተን ይበልጥ ያጠነከርኩህ ስለ ሆነ እነዚህን በዕብሪት ዐመፀኞች የሆኑትን የምትፈራበት ምንም ምክንያት የለም።”


እኔን ግን እግዚአብሔር በመንፈሱና በኀይሉ ሞልቶኛል፤ የእስራኤል ሕዝብ በደላቸውና ኃጢአታቸው ምን እንደ ሆነ አስታውቃቸው ዘንድ በግልጽ ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት ብርታትን ሰጥቶኛል።


የንጉሡንም ቊጣ ሳይፈራ ከግብጽ የወጣው በእምነት ነው፤ በዐይን የማይታየውንም አምላክ እንዳየው ያኽል ሆኖ በዓላማው ጸና።


跟着我们:

广告


广告