Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ በኬባር ወንዝ አጠገብ ወዳለው ወደ ቴል አቢብ መጣሁ፤ ይህም ስፍራ የምርኮኞች መኖሪያ ነበር፤ ባየሁትና በሰማሁት ነገር ሁሉ በመደንገጥ ደንዝዤ በመካከላቸው ሰባት ቀን ቈየሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም በኮቦር ወንዝ አጠገብ በቴልአቢብ ወደሚኖሩት ምርኮኞች መጣሁ፣ በድንጋጤ ፈዝዤም ከእነርሱ ጋራ ሰባት ቀን በመካከላቸው ተቀመጥሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በኮቦር ወንዝ አጠገብ ወደሚኖሩ፥ በቴልአቢብም ወዳሉ ምርኮኞች መጣሁ፥ በዚያ በሚኖሩበትም ሰባት ቀን በመካከላቸው በድንጋጤ ተቀመጥሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በቴ​ል​አ​ቢ​ብም ወደ አሉ፥ በኮ​ቦ​ርም ወንዝ አጠ​ገብ ወደ ተቀ​መጡ ምር​ኮ​ኞች መጣሁ፤ በተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትም ቦታ ተቀ​መ​ጥሁ፤ በዚ​ያም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ስሁ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በቴልአቢብም ወዳሉ በኮቦርም ወንዝ አጠገብ ወደ ተቀመጡ ምርኮኞች መጣሁ፥ በተቀመጡበትም ቦታ ተቀመጥሁ፥ በዚያም ሰባት ቀን በድንጋጤ በመካከላቸው ተቀመጥሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 3:15
10 交叉引用  

ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።


የሥቃዩንም ብዛት ስላዩ ምንም ቃል ሳይናገሩ ከእርሱ ጋር ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት በመሬት ላይ ተቀምጠው ሰነበቱ።


በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን፥ ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።


ስለ ነቢያት በማስብበት ጊዜ ልቤ በሐዘን ይሰበራል፤ አጥንቶቼም ይንቀጠቀጣሉ፤ ከእግዚአብሔር ከቅዱስ ቃሉ የተነሣ፥ በወይን ጠጅ እንደ ተሸነፈ ሰካራም ሆኜአለሁ፤


በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።


በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የእግዚአብሔር ቃል የቡዚ ልጅ ወደ ሆንኩት ወደ ካህኑ ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ ነበረ።


ኪሩቤል ወደ ላይ ተነሡ እነርሱም በኬባር ወንዝ አጠገብ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረቶች ናቸው።


ስለዚህ ተነሥቼ ወደ ሸለቆው ወረድኩ፤ እዚያም በኬባር ወንዝ አጠገብ ባየሁት ሁኔታ የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠልኝ፤ በግንባሬም ወደ መሬት ተደፋሁ፤


ይህም ራእይ ከዚህ በፊት እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ ያየሁትን ይመስል ነበር፤ በኬባር ወንዝ አጠገብ ካየሁትም ራእይ ጋር ይመሳሰላል፤ በዚያን ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ።


ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።


跟着我们:

广告


广告